በነፍሳት አምሳል የተሰሩ ሮቦቶች የወንዴ አበባ ዘርን ወደ ሴቴ አበባ በማሸጋገር የነፍሳትን ሚና መወጣት መቻላቸው ተገለጸ

Source: https://fanabc.com/2018/10/%E1%89%A0%E1%8A%90%E1%8D%8D%E1%88%B3%E1%89%B5-%E1%8A%A0%E1%88%9D%E1%88%B3%E1%88%8D-%E1%8B%A8%E1%89%B0%E1%88%B0%E1%88%A9-%E1%88%AE%E1%89%A6%E1%89%B6%E1%89%BD-%E1%8B%A8%E1%8B%88%E1%8A%95%E1%8B%B4/

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በነፍሳት አምሳል የተሰሩ ሮቦቶች የወንዴ አበባ ዘርን ወደ ሴቴ አበባ በማሸጋገር የነፍሳትን ሚና መወጣት መቻላቸው ተገልጿል።

ሰው ሰራሽ ነፈሳቶቹ ምንም እንኳ ማር በመስራት ንቦችን ባይተኩ እንኳ የወንዴ አበባ ዘረን ወደ ሴቴ የአበባ ዘር በማሸጋገር የተዋጣላቸው መሆኑ ነው የተገለጸው።

ደልፊት በተባለው የኔዘርላንድ ዩንቨርሲቲ ተመራማሪዎች የተሰሩት አዲሶቹ የቴክኖሎጂ ውጤቶች 33 ሴንቲሜትር ርዝመት ያለው ክንፍ እና 29 ግራም ክብደት ያላቸው ሲሆን፥ በሰከንድ 17 ጊዜ ያህል ክንፎቻቸውን በማርገብገብ በአየር ላይ ለመዋል ይችላሉ ተብሏል።

ሰው ሰራሽ ነፍሳቶቹ ባትሪ በመጠቀም ለ6 ደቂቃዎች ያህል በአየር ላይ በመቆየት 1 ኪሎሜትር ያህል ርቀት የሚሸፈን በረራ ለማድረግ እንደሚችሉም ነው የተገለጸው።

በረራቸውን በመቆጣጠር ወደተለያዩ አካባቢዎች ለምብረር እንደሚቻሉም ታውቋል።

አሁን ላይ የተላለያዩ የጸረ ነፍሳት ኬሚካሎች በዓለም አቀፍ ደረጃ በሰፊው አገልግሎት ላይ እየዋሉ መሆኑን ተከትሎ የነፍሳቶች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱን ዘገባው አስታውሷል።

በዚህም በዓለም አቀፍ ደረጃ 360 ያህል የነፍሳት ዘርያዎች ከገጸ ምድር የመጥፋት እደጋ እንዳዣበበባቸው ተጠቁሟል።

ነፍሳቱ 80 በመቶ ያህል እጽዋቶችን የወንዴ አበባን ዘር ወደ ሴቴ አበባ በማሸጋገር የእርሻውን ዘርፍ ምረትና ምርታማነት በማሳደግ በኩል አስዋጽኦ እንዳላቸውም ነው የተገለጸው።

አዲሶቹ የፈጠራ ውጤቶች ከላይ የተጠቀሰውን ስጋት ለመፍታት ተስፋ የተጣለባቸው ሲሆን፥ ተፈጥሯዊዩን መንገድ በሰው ሰራሽ ለመተካት ከፍተኛ ኢኮኖሚ ከመጠየቁም በሻገር ተጨማሪ ጥናት ማካሄድ አስፈላጊ መሆኑን ዘገባው ያስረዳል።

ምንጭ፦ thenextweb.com

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.