በአልጀሪያ ሆስፒታል ውስጥ በተነሳ እሳት 8 ህጻናት ሞቱ

Source: https://fanabc.com/2019/09/%E1%89%A0%E1%8A%A0%E1%88%8D%E1%8C%80%E1%88%AA%E1%8B%AB-%E1%88%86%E1%88%B5%E1%8D%92%E1%89%B3%E1%88%8D-%E1%8B%8D%E1%88%B5%E1%8C%A5-%E1%89%A0%E1%89%B0%E1%8A%90%E1%88%B3-%E1%8A%A5%E1%88%B3%E1%89%B5-8/

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 13 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአልጀሪያ ሆስፒታል ውስጥ በተነሳ እሳት 8 ህጻናት መሞታቸው ተነገረ።

አደጋው በምስራቃዊ የሃገሪቱ ክፍል በሚገኝ ሆስፒታል የህጻናት ክፍል ውስጥ የተነሳ ነው ተብሏል።

ከአደጋው 11 ህጻናትን መታደግ መቻሉን የሆስፒታሉ ቃል አቀባይ ተናግረዋል።

የእሳቱ መንስኤ እስካሁን ያልታወቀ ሲሆን፥ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችም እሳቱን ለመቆጣጠር እየሞከሩ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኑረዲን በደዊ ሁኔታውን የሚያጣራ ቡድን ወደ ስፍራው መላካቸው ተሰምቷል።

 

 

ምንጭ፦ ሲ ጂ ቲ ኤን

 

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.