በአሓዳዊ ፖለቲካ አቀንቃኞች ላይ ቀዝቃዛ ውኃን የቸለሰው ኦዲፒ ‘በፌዴራሊዝም አልደራደርም’ ሲል ምን ማለቱ ነው?

Source: https://mereja.com/amharic/v2/95226

BBC Amharic
የሰሞኑ የኦዲፓ መግለጫ እንደዋዛ አልታለፈም፤ ለሰፊ የማኅበራዊ ውይይት በር ከፍተ እንጂ። ‘በፌዴራሊዝሙ አንደራደርም’ የሚለው ሐሳብ በተለይም በአሓዳዊ ፖለቲካ አቀንቃኞች ላይ ቀዝቃዛ ውኃን የቸለሰ ይመስላል።
ኾኖም መግለጫው ለተከፈተ ዘመቻ ምላሽ እንደሆነ በኦዲፒ ተገልጿል፤ ዘመቻው በማን፣ መቼና የት እንደተከፈተ ለይቶ ባይጠቅስም።
ይህ በፌዴራሊዝም ላይ ተከፈተ የተባለው የሐሰት ዘመቻ ሁለት ግብ እንደነበረው የኦዲፒ መግለጫ ጨምሮ ያወሳል።
ኢንጂነር ይልቃል ጌትነትና አቶ ኤፍሬም ማዴቦ
‘የፌዴራል ሥርዓቱ ከዛሬ ነገ መፍረሱ ነው በሚል ብሔር ብሔረሰቦች በጥርጣሬ እንዲመለከቱት ማድረግ ሲሆን ሌላው ደግሞ’ ተጨማሪ መብት እንደሚያገኝ እየጠበቀ ያለውን የኦሮሞን ሕዝብ’ እንኳንስ ተጨማሪ መብት ይቅርና ‘ከዚህ ቀደም ያገኘኸውንም ልታጣ ነው’ በሚል ማደናገር ነው ሲል የዘመቻውን ግብ ያትታል።
ለመኾኑ መግለጫዉ ባለፉት ቀናት በሕዝብ ዘንድ ሰፊ መነጋገሪያ ለምን ኾነ? በዚህ ወቅት ይህን መግለጫ ማውጣትስ ለምን አስፈለገ? በተገዳዳሪ ፓርቲዎች ዘንድ መግለጫው ምን ስሜት ፈጠረ? ቢቢሲ የአርበኞች ግንቦት ሰባትንና የኢሃን አመራሮችን አነጋግሯል።
‘ሕዝቡ በምኞት ቀውስ ውስጥ ነው’
ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት መግለጫው አነጋጋሪ የሆነው በርካታ ሕዝብ ዶ/ር ዐቢይ አገሩን አንድ አደርጋለሁ የሚሉትን ነገር እንደ ትግል አጀንዳ የምር በመቁጠሩ ይህን ተከትሎ የመጣ “የምኞትና የፍላጎት ቀውስ” ነው ይላሉ።
ዶ/ር ዐቢይ የሚናገሩትን ብቻ በማየት ብዙ ሰዉ ለዉጡ ሥር ነቀል ነዉ ብሎ አምኖ ነበር። ነገር ግን አሁን የኦዲፒ ትክክለኛ አቋም በተለየም በፌዴራሊዝም ዙርያ የቱ ጋር እንደሆነ ሲታወቅ በሕዝቡ ዘንድ የምኞት ቀውስን እንዳስከተለ ይገምታሉ።
”እንደ ሕዝብ ከደረቅ ሐቅ ይልቅ ምኞታችንን የማመን ደዌ ተጸናውቶናል” ይላሉ።

Share this post

2 thoughts on “በአሓዳዊ ፖለቲካ አቀንቃኞች ላይ ቀዝቃዛ ውኃን የቸለሰው ኦዲፒ ‘በፌዴራሊዝም አልደራደርም’ ሲል ምን ማለቱ ነው?

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.