በአመፅና በትጥቅ ጥቃት ሳቢያ በሞሮኮ ኩባንያዎች ላይ ለሚደርስ ጉዳት የኢትዮጵያ መንግሥት ካሳ ለመስጠት ግዴታ ሊገባ ነው

Source: https://mereja.com/amharic/v2/75426

በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን በሚያፈሱ የሞሮኮ ኩባንያዎች ላይ ድንገተኛ በሆነ ሕዝባዊ አመፅ፣ የትጥቅ ጥቃት ወይም ተመሳሳይነት ባላቸው ክስተቶች ምክንያት ጉዳት ቢደርስ የጉዳት ካሳና መልሶ ማቋቋሚያ ክፍያን የሚያስገድድ ስምምነት መንግሥት ሊፈጽም ነው።
በኢትዮጵያና በሞሮኮ መንግሥት መካከል ኢንቨስትመንትን ለማበረታታትና ጥበቃ ለማድረግ የተፈረመውን ይህንን ስምምነት ለማፅደቅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከሳምንት በፊት የተላከ ሲሆን፣ የምክር ቤቱ የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ስምምነቱን አስመልክቶ በአሁኑ ወቅት ዝርዝር ምርመራ በማድረግ ላይ ይገኛል። በሕዝባዊ አመፅ፣ በትጥቅ ውጊያ ወይም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክንያት በሞሮኮ ኢንቨስትመንት ላይ ለሚደርስ የጉዳት ካሳና መልሶ ማቋቋሚያ የመስጠት ግዴታን በመንግሥት ላይ የሚጥለው ይህ ስምምነት፣ በተጨማሪም የመንግሥት ኃይሎች ወይም ባለሥልጣናት በሰጡት ትዕዛዝ ወይም በፈጸሙት ድርጊት ምክንያት፣ እንዲሁም ሁኔታዎች ሳያስገድዱ በመንግሥት ኃይሎች ወይም ባለሥልጣናት በኢንቨስትመንት ላይ ውድመት ወይም ጉዳት የደረሰ እንደሆነ ተመጣጣኝና ፍትሐዊ ካሳ የመክፈል ግዴታን ይጥላል።
በዚህ መንገድ ለሚደርሱ ጉዳቶች የሚሰጠው ካሳ ያላግባብ መዘግየት እንደማይኖርበት፣ የካሳ ክፍያ የተሰጠው ኩባንያም ክፍያውን በነፃነት አግባብነት ባለው የውጭ ምንዛሪ በመቀየር ከአገር የማስወጣት መብት እንደሚኖረው የስምምነቱ ይዘት ያስረዳል። ነገር ግን የካሳ ክፍያን ወይም በማንኛውም ወቅት ከኢንቨስትመንቱ የተገኘ ትርፍን በውጭ ምንዛሪ ቀይሮ የማስወጣት መብትን ስምምነቱ ቢፈቅድም፣ ሒደቱ በልዩ ሁኔታ በአገር የማክሮ ኢኮኖሚ ሥርዓት በተለይም በገንዘብ ምንዛሪ ፖሊሲ ላይ ከፍተኛ ችግር የሚያስከትል ከሆነ ከአድልኦ በነፃ መንገድ የገንዘብ ዝውውሩ ላልተወሰነ ጊዜ ሊታገድ እንደሚችል፣ ሆኖም ዕገዳው ሁኔታው ከሚወሰደው ምክንያታዊ ጊዜ በላይ መቀጠል እንደማይችል

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.