በአማራ ክልል ኦሮሞኛ መሰጠት የለበትም የሚሉ በስሜት ሳይሆን በመረጃ ይከራከሩን – ግርማ ካስ

Source: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/89083

በቅርቡ እኔም ያለሁበት የምሁራንና አክቲቪስቶች ስብስብ ለአቶ ገዱ አንዳርጋቸው በአማራ ክልል ከአማርኛ ከእንግሊዘኛ በተጨማሪ ሶስተኛ ቋንቋ እንዲሰጥና ሶስተኛው ቋንቋም አሮምኛ ከሆነ በላቲን ሳይሆን በግእዝ ፊደል እንዲጻፍ የሚጠይቅ ፣ ከአባሪ ሰነዶች ጋር በማያያዝ ደብዳቤ ጽፏል። ደብዳቤው ከቀድሞ የኦህዴድ አመራርና የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት የተከበሩ ግርማ ወልደጊዮርጊስ ይፋዊ ድግፍ ያገኝ ሲሆን ከሁሉም ማእዘናት ኢትዮጵያዊያን አዎንታዊ ምላሽ እየሰጡበት ነው። ሆኖም […]

Share this post

One thought on “በአማራ ክልል ኦሮሞኛ መሰጠት የለበትም የሚሉ በስሜት ሳይሆን በመረጃ ይከራከሩን – ግርማ ካስ

 1. አዛኝ ቅቤ አንጓች!
  ….ኦሮምኛ ቋንቋ ዓላማው የአማራን የክልል ሕዝብ መጥቀም ነው። ሶስተኛ ቋንቋ ማወቁ በምንም መሰፈርት የሚጠቅም እንጂ የሚያከስር አይደለም።፡
  ባይሳ ዋቆያ….እኔም አማርኛን የማወራውና የምጽፈው፣ ያቀድኩትን ዓላማ ከግብ ለማድረስ ይጠቅመኛል ብዬ እንጂ አማርኛ ተናጋሪውን ህዝብ ለማስደሰት አይደለም! “በ1940 ዎቹ መጀመርያ ላይ የወለጋ ገዢ የነበሩ ደጃዝማች መኮንን ደስታ፣ ጠቅላይ ግዛቱን እየዞረ ሲጎበኝ፣ በግዕዝ ፊደል የተጻፈው ኦሮሚኛ መጽሃፍ ቅዱስና መንፈሳዊ መዝሙሮች በጠቅላይ ግዛቱ መስፋፋታቸውን ከተረዳ በኋላ “ጋልኛን ለመሳሰሉ ቋንቋዎች የግዕዝ ፊደልን መጠቀም ፊደሉን ማርከስ ነው” ብሎ ያወጣው መመርያ፣ ቋንቋው “ተፈጥሮያዊ” በሆነ መንገድ አድጎ አገራዊ እንዳይሆን ትልቅ ዕንቅፋት የነበሩት የቋንቋው ባለቤቶች ራሳቸው ለመሆናቸው አመላካች ይመስለኛል።በኦሮሞና በአማራ ህዝቦች መካከል ያለው የመቀራረብና የመዋደድ ሁኔታ በታሪካችን ውስጥ ታይቶ የማይታይ ደረጃ ላይ የደረሰው ባለፉት አሥር ዓመታት ውስጥ ነው።(!?)
  ….አሁን ሀገራችን የገጠማት ችግር የቋንቋ ነው ወይስ የስርዓት?
  ባይሳ ዋቆያ” አዎ! እንደ አንድ ዜጋ የኢትዮጵያ ህዝብ አጥሮት እየተቸገረ ካለው ወርቃማ ጊዜ ቆርሶ ኦሮሚኛን በመማር
  እንዲቃጠል ማድረግ “ኃላፊነት የጎደለው” መሆኑን ማስገንዘባቸውና፣ አገሪቱ የተቆለለባትን ዓለም ዓቀፋዊ ዕዳ መክፈል አቅቷት በመጨነቅ እያለች፣ “በዕንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ” እንዲሉ፣ ኦሮሚኛን ለማስተማር በጀት መመደብ አስፈላጊ አይደለም ሲሉ የዜግነት ግዴታቸውን የተወጡ ይመስላል።
  ….. ኦሮምኛ ቋንቋን በአማራ ክልል እንዲስያተምሩ ከመጠየቃቸው በፊት በኦሮሚያ ክልል በየጊዜው ስለሚፈናቀሉ፣ ውክልና ስለተነፈጉ፣ባህል ወግና ማንነታቸውን ተነፍገው ራሳቸውን በራሳቸው እንዲያስተዳድሩ ስላልተፈቀደላቸው አማራዎች ለምን ፊርማ ማሰባሰብ …..”
  *ባይሳ ዋቆያ “ኦሮምኛ ምናልባት ከአማርኛ እኩል በሁሉም ክልሎች የመግባቢያ ቋንቋ አይሆን እንደሁ እንጂ፣ ኦሮሚኛ በብዙ የኢትዮጵያ ብሄሮች መካከል የመግባቢ ቋንቋ ሆኖ እያገለገለ ነው። ከዚያም በላይ የኦሮሚያ ክልል በቆዳ ሰፋትና በህዝብ ብዛት ብቻ ሳይሆን በአገሪቱ ውስጥ ለሚመረቱት አላቂና ዘላቂ ሸቀጦች ትልቁን ተጠቃሚ ገበያተኛና ገበያ አቅራቢ ስለሆነ፣ ሸቀጦቻቸውን በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ለመሸጥ ወይም ሠርተው ለማደር ለሚፈልጉ የሌላ ብሄር ቋንቋ ተናጋሪ ዜጎች የኦሮሚኛን ቋንቋ በመጠኑም ቢሆን ማወቅ ለኑሮአቸው ስኬታማነት ትልቅ አስተዋጽዖ ይኖረዋል።”
  ……”ኦሮምኛ ቋንቋ መማር አለብን የሚል ፍላጎት ከየትኛው የአማራ ግዛት ነው የመጣው?
  ባይሳ ዋቆያ”የዲያስፐር አደራዳሪና ህወሓት አትንኩ ጠቅሞናል ሸምጋይ”የኢትዮጵያ ሰፊ ህዝብማ ላለፉት ሰላሳ ዓመታት በኦሮሞዎች የላቲን ፊደል መጠቀም ቅሬታ አላሰማም። የኦሮሞ ህዝብ ደግሞ በሰላሳ ዓመት ጊዜ ውስጥ ቋንቋውንና ሥነ ጽሁፉን አዳብሮ በታሪኩ ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ እየተደሰተ ነው። ባለፉት ሁለት መቶ ዓመታት ውስጥ የሳባውያንን ፊደልን ተጠቅሞ የተጻፈ አንድ የኦሮሚኛ መጽሃፍ ቅዱስ ብቻ ሲሆን፣ ባለፉት ሰላሳ ዓመታት ግን በሺዎች የሚቆጠሩ ሥነ ጽሁፎችን አበርክቷል። ይህንን የኦሮሞን ህዝብ ያስደሰተውን ሂደት ነው እንግዲህ ለጥቂት ግለሰቦች ደስታ ተብሎ እንድንተወው ፕሮፌሰር የሚወተውቱን።(ከኦሮሞው በላይ ያፏጨው ግርማ)

  **ዲያስፐር ክልላዊ ልሂቃናዊ የፖልቲካ ተንታኞች…. በ፪፲፻፱ ዓ.ም የፍቅር፡ የሃይማኖትና የልመና ደብዳቤ ከደረሳቸው የመጀመሪያው ኅይለመልስ ደስለኝ ነበሩ ያልጻፈላቸው የለም አንዱንም ሳያነቡና ሳይመለሱ ተነሱ። አሁን ለማና ደጉ ተረኛ ናቸው ይህ ዲያስፐር ወይ ሊያስበላቸው ነው ወይ ሀገር ሊያባላ ነው። እንዲህ መልካም ራዕይ ያለው ሰብሰብ ብሎ ኢህአዴግ ቢሮ አይሄደም። ምድረ ደንባራ አንዱ ክልል ተብዬ በላቲን አንዱ በግዕዝ እየጻፈ ማን ሊያስተርጉም ነው? ሁለቱም ተማሪዎች እኩል ማርክ ያገኛሉ፡ቋንቋው የፌደራል ቢሆን ስንት ወረቀት ሊታተም ነው? ለመሆኑ የደቡብ ክልል የምትሉትን ቆርጣችሁ ኢትዮ ሱማሌና አፋርን ጥላችሁ በልዩ ጥቅማጥቅም አዲሳበባን ፊንፌኔ ብላችሁ ሌላወን መጤ ማለታችሁ ዋጋ ያስከፈለውን ያህል አሁን ሁለቱ ትልቅ ሕዝቦች ትልቅ ብሔሮች ትልቅ ክልሎች እያላችሁ መንሳነስ በእርግጥ ኦሮሞን ልትጥቅሙ ነው ወይንስ የአፍሪካ ትልቁ ቋንቋ ለማሰኘት ፴፬ ሚሊየን አማራ አብሮ ለማጨቅ ነው? ምነው ኦህዴድ አዲስ አበባ የሁሉም ናት አላሉም!? ከኢትዮ ሱማሌ በቋንቋ በሃይማኖት አንድ ሆነው ተጋብተው ተዋልደው ባይጣሉና በሜንጫ አንገት ባይቀነጣጠሱ ኦህዴድዶች ብሔርን ከመታወቂያ ይፍቃሉን?
  *ባይሳ ዋቆያ “ከኢህአዴግ ጋር እንደራደር ሲል ክልልና ቋንቋ የሰጠውን ጌታው እንዳይሄድ አማራ እንዳይነግስ ነው። በኢትዮጵያም የትግርኛና አማርኛ ተናጋሪዎች ለቋንቋቸው የሚስማማቸውን ፊደል ለመሸመት ወደ ፊደል ገበያ ሲወጡ ተስማሚ ሆኖ ያገኙትን የሳባውያን ፊደልን ነው ሸምተው የተመለሱት። የሸመቱትም ፊደል ለቋንቋቸው በጣም ተስማሚ ሆኖ ስላገኙት ይኼው እስከዛሬ ድረስ ያላንዳች ማጉረምረም እየተጠቀሙበት ነው። የኦሮሞ ህዝብ ግን ወደ ቋንቋ ገበያ ወጥቶ የመረጠውን የመሸመት ዕድል ስላልነበረው የፊውዳሉ ሥርዓት የመረጠለትን የሳባውያን ፊደል ተውሶ ለሁለት ምዕተ ዓመት ከተጠቀመበት በኋላ፣ በነጻ የቋንቋ ገበያ ላይ ወጥቶ የሚስማማውን የመሸመት አጋጣሚ እንዳገኘ፣ ወዲያውኑ የላቲንን ፊደል ሸምቶ መጠቀሚያ ካደረገ ይኸውና ሶስት አሥርት ዓመታት ሊሆነው ነው። እስካሁን ድረስ ተውሰን ያመጣነው የላቲን ሸቀጥ አንዳችም ዓይነት ጎጂነት የሌለውና ለቋንቋው ዕድገት በጣም ተስማሚ ሆኖ ስላገኘነው በሂደት ውስጥ ሌላ የተሻለ እስክናገኝ ድረስ እየተጠቀምንበት እንቀጥላለን።
  ፕሮፌሰር ኅይሌም ሆነ ሌሎች ተመሳሳይ አስተሳሰብን ለሚያስተናግዱ ወገኖቼን ሁልጊዜም እየጠየቅሁ ግን ደግሞ መልስ ያላገኘሁለትን ጉዳይ ደግሜ ልጠይቅና፣ ኦሮሞዎች በላቲን ፊደል መጠቀም ከጀመሩ ይሄው ሰላሳ ዓመት ሊሞላው ሲሆን፣ ይህን በሚያክል ጊዜ ውስጥ በሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦችና በኢትዮጵያ ራስዋ ላይ የደረሰው ጉዳት ምን እንደሆነ ዕቅጩን ቢነግሩን ለውይይቱም የሚያመች ይመስለኛል። አለበለዚያ ግን ስንት አንገባጋቢ የሆነ ያገሪቱን ህዝቦች ሰላምና ህልውናን የሚፈታተን አገራዊ ቀውስ እየተስተዋለ ባለበት ባሁኑ ሰዓት ዋናውን ችግር መጋፈጥን ፈርቶ አላስፈላጊ ወደሆነ ጥያቄ የህዝብን ቀልብ ለመሳብ መሞከር ኃላፊነት የጎደለው አቀራረብ ይመስለኛል።”
  *** አዳሜ ብሔራዊ እርቅ…ብሔራዊ ራዕይ.. ብሔራዊ ፓርቲ..ኅብረብሔራዊ አጀንዳ… ተቃዋሚ እያለ ቱሪናፋውን እየበጠረቀ፡ የጎንዮሽ እየተላፋ በአዳራሽ እያጨበጨበና ሚዲያ ላይ ሲደነፋ ውሎ እያደረ ኢህአዴግን እንታገላለን ይላል? ፕ/እስቅአኤል ሌንጮ ለታን ሲጠይቀው ለመሆኑ ኦነግ ባለፉት ፵፫ ዓመት ከትግል ለኦሮሞ ምን አተረፍኩ ይላል? ሌንጮ ለታ” ሃሌ ሉያ ያልጠበቅነውን መሬት አገኘን” ጅዋር መሐመድ “አማሮቹ ሚዲያ ላይ የምሄደው ወድጃቸው መሰላችሁ ላስተምራቸውና አንድ የኦሮሞ ምሁር አለ ብሎ ወጣቱ እንዲነሳሳ ነው” እነኝህም ምሁር ተብዬ ፎጋሪዎች አትርሱን ባይ ቱልቱላዎች ናቸው። አሁን የሚበላ የለ… መሄጃ ያጣው ኦሮሞና አማራ ገበሬ እንኳ ቋንቋ ሊያስብ ማንነቱ ጠፍቶት መክኗል ባክኗል፡ በነፍስ አውጭኝ ዘመን የቋንቋ ጠቢባን ይቆላሉ? ይልቁንም ውሃ አቅርቡ፡ ምግብ ለምኑ፡የመማሪያ መሳሪያ(እርሳስና ደብተር) አቅርቡ። ሜንጫ አትሳሉ ሕዝቡን ባልበላ አንጀቱ ስቃይና መከራ ማባዣ አትቆፍሩ፡የኦሮሞ ሊሂቃን ፌደራላዊ የቋንቋ ሥርዓቱ በዙ መብት ሰጥቶናል ብለዋል።እናንተ እነማን ናችሁ!? ልብ ካላችሁ የከብት ጋጣ ክልልን አፍርሳችሁ ድልድይ ሥሩ(አትችሉም)..ሕዝቡ ሲቀራረብ ከቁቤ በፊትም በኋላም ፅዋ እየጠጣ፡በዕድር ተሳስሮ፡ እቁብ እየጣለ ይገበያያል ይጋባል ይዋለዳል።ችግርና ሽብር ፈጣሪ ቡድን አትሁኑበት ነጻነት!!!

  Reply

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.