በአማራ ክልል የህዋት አገዛዝ እስረኞችን ከ7 እስከ 10 ሺ ብሮችን አስከፍሎ በመልቀቅ ገንዘብ በመሰብሰብ ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ

Source: http://amharic.abbaymedia.com/archives/27455

ለትንሳኤ ሬድዮ የደረሰዉ መረጃ እንደሚያመለክተዉ በአማራ ከልል በተለይ በፍኖተ ሰላም በጅጋ በጎንደር እና ባህር ዳር ከህዝባዊ እቢተኝነት ንቅናቄ ጋር በተያያዘ ታስረዉ ከነበሩ ወጣቶች መሀል ከ 7 እስከ 10 ሺ ብር መክፈል ከሚችሉት ዉስጥ የተወሰኑትን ካለፈዉ ሳምንት ጀምሮ እየለቀቀ መሆኑን ያመለክታል። እረቡዕ እለት መጋቢት 13 2009 አ.ም ከፍኖተ ሰላም ማረሚያ  ቤት 17 ወጣቶች ሰባት ሰባት ሺ ብሮችን በመክፈል መለቀቃቸዉን እንዲሁም ከጅጋ ማረሚያ  ቤት 15 ወጣቶች አስር አስር ሺ ብሮችን በመክፈል መለቀቃቸዉን የዉስጥ ምንጮቻችን ገልፀዋል።

  ከፍኖተ ሰላም ማረሚያ ቤት ከተለቀቁት መሀከል አንድ ወጣት “አንተ መለቀቅ አልነበረብህም ተብሎ በድጋሚ መታሰሩ የታወቀ ሲሆን ለመለቀቂያ የከፈለዉ 7 ሺ ብር ሳይመለስለት እንደቀረም ታዉቋል፡፤ የቀሩት ወጣቶችም ተመልሰዉ እንደማይታሰሩ ምንም ዋስትና ስለሌላቸዉ በስጋት ዉስጥ ይገኛሉ፤አንዳንዶች እንደዉም አካባቢያቸዉን እየለቀቁ ናቸዉ በማለት ያካባቢዉ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

Share this post

2 thoughts on “በአማራ ክልል የህዋት አገዛዝ እስረኞችን ከ7 እስከ 10 ሺ ብሮችን አስከፍሎ በመልቀቅ ገንዘብ በመሰብሰብ ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ

  1. 10000.00 birr birek new !gena zer manzerun kitun y…Galebew yehen kezenam amahara/temeketegna/nefetam. Kef yelal gena yetegrie zena!!!

    Reply
  2. As you well recommended by our renown pm, who recently nominated for honorary doctorate degree offer from Tampere university”sefedikin yzeh zure “lemagn amahara!!!

    Reply

Post Comment