በአማራ ክልል የሚገኙ ት/ቤቶች 84 በመቶ ያህሉ ከደረጃ በታች ናቸው ተባለ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/176218

በአማራ ክልል የሚገኙ ት/ቤቶች 84 በመቶ ያህሉ ከደረጃ በታች ናቸው ተባለ
በአማራ ክልል ከሚገኙ ት/ቤቶች 84 በመቶ ያህሉ ከደረጃ በታች በመሆናቸው የት/ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል በትኩረት እየተሠራ መሆኑን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡
ትምህርት ቤቶች በአጠቃላይ ኢንስፔክሽን ስታንዳርድ መሰረት በግብዓት፣ ሂደቶችና ውጤቶች ሲለኩ ደረጃ 3 እና ከዚያ በላይ ያሉ ት/ቤቶች ደረጃቸውን የጠበቁ የሚባሉ ሲሆን፣ ከዚህ በታች የሆኑት ደግሞ ከደረጃ በታች በሚል ይካተታሉ፡፡

በዚህ መለኪያ መሠረት በአማራ ክልል ከ84 በመቶ በላይ የሚሆኑ ት/ቤቶች ደረጃ 1 እና 2 ላይ የሚገኙ በመሆናቸው ብዙ መሠራት እንዳለበት የክልሉ ትምህርት ቢሮ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ቢያዝን ለኢቲቪ ተናግረዋል፡፡
የዘርፉን ችግር ለመቅረፍ ጥራት ያላቸውን ትምህርት ቤቶች በሁሉም አካባቢዎች ተደራሽ ማድረግ እና በመሠረተ ልማት ማበልጸግ ላይ ትልቅ ሥራ መሠራት እንዳለበት አቶ ጌታቸው ገልጸዋል፡፡
ከደረጃ በታች የሆኑ ት/ቤቶች በሁሉም አካባቢዎች ላይ የሚገኙ ቢሆንም፣ በሰሜን ጎንደር እና ዋግ ኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በሚገኙ ወረዳዎች ችግሩ በጣም የከፋ በመሆኑ በሁለቱ ዞኖች 12 ት/ቤቶች ተለይተው በባለሀብቶች ለመሥራት እንቅስቃሴ መጀመሩ ተገልጿል፡፡
በመሆኑም በሰሜን ጎንደር ዞን 6 እና በዋግ ኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር 6 ት/ቤቶች የተለዩ ሲሆን፣ ከኅዳር ወር መጨረሻ ጀምሮ በባለሀብቶች እንዲሠሩ ለማድረግ እየተሠራ ነው ብለዋል አቶ ጌታቸው፡፡
ክረምት በመሆኑ ለግንባታ አመቺ አለመሆኑ፣ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ት/ቤቶች ቶሎ አለመለየታቸው፣ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ቀድመው ባለመጠናቀቃቸው ግንባታው ቶሎ ላለመጀመሩ በምክንያት ተገልጸዋል፡፡
የክልሉ ትምህርት ቢሮ ከአማራ አቀፍ ልማት ማኅበር ጋር

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.