በአምቦ ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች የእርቅ ስነስርዓት ተካሄደ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/76130

በአምቦ ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች የእርቅ ስነስርዓት እየተካሄደ ነው

በእርቅ ስነስርዓቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የአምቦ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ታደሠ ቀነአ ተማሪዎች የራሳቸውን ደስታ በራሳቸው ማምጣት እንደሚኖርባቸው ገልጸዋል።
የዛሬ ሳምንት በዩኒቨርስቲው ይህ ሁኔታ እንዳልነበረና ዛሬ ግን አብረው ተቀምጠው መነጋገር በመቻላቸው የሰላም አየር እንዲነፍስ መደላድል መፍጠሩን ተናግረዋል።
“ስንሰማማና አንድ ስንሆን የማንችለው ነገር የለምና አንድ ሆነን ሰላማችንን እንጠብቅ ” ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል ።
ከጥል ምንም ትርፍ እንደማይኖረው ጠቅሰው የአምቦ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ልዩነቶችን አቻችለው ለሌሎች አርዓያ መሆን እንደሚጠበቅባቸውም ዶክተር ታደሠ ለኢዜአ ገልጸዋል።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.