በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ በማንና ለምን እንደ ተከፈተ የማይታወቅ የት/ት ክፍል (ዲፓርትመንት) ተገኘ!!

Source: https://mereja.com/amharic/v2/71787

በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ በማንና ለምን እንደ ተከፈተ የማይታወቅ የት/ት ክፍል (ዲፓርትመንት) ተገኘ!!

በአርባምንጭ ቴክኖሎጂ ኢንስትቲውት ስር ዩኒቨርስቲውና ትምህርት ሚንስቴር የሚያውቋቸው የተለያዩ የትምህርት ክፍሎች እንዳሉ ቢታወቅም ዛሬ የተሰማው ዜና ግን አስገራሚም አሳፋሪም ሆኗል፡፡ Production Engineering በሚባል ትምህርት ክፍል ውስጥ እስከ አምስተኛ ዓመት የደረሱ ተማሪዎችን እያስተማረ የቆየው የአርባምንጭ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በዛሬው ዕለት ከዩኒቨርስቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት በተሰማው ወሬ ይህንን ትምህርት ክፍል እሳቸውም ሆኑ ሌሎች የዩኒቨርስቲው የበላይ አመራሮች እንደማያውቁት ተገልጿል፡፡
በዚህም መነሻነት የትምህርት ክፍሉ ከአንደኛ እስከ አምስተኛ ዓመት ያሉ ተማሪዎች በዛሬው ዕለት በዩኒቨርስቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ ሰላማዊ ሰልፍ ያደረጉ ሲሆን ከተማሪዎቹ እንደተገኘው መረጃ ከሆነ ስለ ትምህርት ክፍሉ የጠራ መረጃ ስጡን አለበለዚያ በማይታወቅ ዲፓርትመንት አንማርም በማለት በተለያዩ ጊዜያቶች አቤቱታቸውን ለዩኒቨርስቲው አመራሮች እያቀረቡ የቆዩ ቢሆንም የትምህርት ክፍሉ ኃላፊ የሆኑት አቶ አታክልቲ ትምህርት ክፍሉ ከሌሎች ትምህርት ክፍሎች የተሻለ እንደሆነና ሲመረቁም ሜቴክ እንደሚቀጥራቸው በመናገር ሲያታልሏቸው እንደነበረ ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም ተማሪዎቹ በዚህ ዓመት ወደ ተለያዩ ተቋማት practice ወጥተን ለመስራት የተመደብን ብንሆንም የሄድንባቸው ተቋማት በሙሉ production Engineering የሚባል ትምህርት ክፍል አናውቅም በማለት እንደመለሷቸው ተናግረዋል፡፡ በዩኒቨርሲቲው ይህ ዲፓርትመንት ሲከፈት ጀምሮ አሻጥር ያለበትና ላልተገባ ጥቅም ተብሎ የተከፈተ መሆኑን ዘግይተው ማወቃቸውን ተማሪዎቹ አክለው ተናግረዋል።
በዚህ ጉዳይ ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንትን ጨምሮ ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በዛሬው እለት ሰልፍ የወጡ የትምህርት ክፍሉን ተማሪዎችን በመሰብሰብ ያነጋገሩ ሲሆን ይህ ዲፓርትመንት በዩኒቨርስቲው ውስጥ እንዳለ እንደማያውቁ አመራሮቹ ለተማሪዎች በድጋሚ ተናግረዋል፡፡ የዩኒቨርስቲው

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.