በአርቲስት ሃጫሉ ሞት ሳቢያ እየተካሄደ ያለው የዘር ማጥፋት የሀብት ውድመት አረመኔያዊ ተግባር በእጅጉ አሳስቦናል – የዓለም አቀፍ የአማራ ህብረት 

Source: https://www.zehabesha.com/amharic/archives/107568

**የዓለም አቀፍ የአማራ ህብረት ወቅታዊ መግለጫ** በዚህ ታሪካዊ ወቅት በአገራችን በኢትዮጵያ በየቦታው በዘርና በሃይማት ማንነት ላይ ያነጣጠሩ፣ ሕይወት በመቅጠፍ፣ አንጡራ ንብረታቸውንና የእምነት ተቋማትን በማውደም እየተካሄዱ ያሉትን እጅግ ዘግናኝ ጥፋቶች በከፋ ሀዘንና በተሰበረ ልብ እንዲሁም በጥልቅ ወገናዊነት ቁጭት በቅርብ እየተከታተልነው እንገኛለን። ይህ በከፍተኛ ወንድማዊ ፍቅር የምንመካበትን የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን በመሰሪዎች ሴራ መገደልን ተከትሎ በተቀነባበረ መንገድ እየትካሄደ ያለው ወገንን ከወገን በማጨፋጨፍ ሕዝብና ሀገርን የመበታተን ሴራ፣ በሀገራችን ታሪካዊ የውጭ ጠላቶችና በምንደኛ የውስጥ ጉዳይ አስፈጻሚዎች መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው። በየአካባቢው የስም ዝርዝር በመያዝ በአብዛኛው በማንነታቸው ምክንያት ብቻ ሕይወታቸውን እየቀጠፉ ንብረቶቻቸውን ያወደሙት እኩያን ሀገሪቱን በመዝረፍ፣ ሕዝብን በግፍ ዘር በማጥፍት፣ ለስደትና ለሞት ሲዳርጉ የቆዩና በተለይም በአማራ

The post በአርቲስት ሃጫሉ ሞት ሳቢያ እየተካሄደ ያለው የዘር ማጥፋት የሀብት ውድመት አረመኔያዊ ተግባር በእጅጉ አሳስቦናል – የዓለም አቀፍ የአማራ ህብረት  appeared first on ዘ-ሐበሻ: ZeHabesha Latest Ethiopian News Provider.

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.