በአሶሳ ዩኒቨርስቲ በተማሪዎች ላይ በደረሰው እና እየደረሰ ባለው ጉዳት ከአብን የተሰጠ መግለጫ- አብን

Source: https://mereja.com/amharic/v2/68817


*****
ከሰሞኑ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ዩኒቨርሲቲ በተነሳ ግጭት እስከ አሁን ባለን መረጃ መሰረት የ3 ተማሪዎች ሕይወት ማለፉንና ከ40 በላይ ተማሪዎች ቀላልና ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው፤ ሌሎችም ተማሪዎች በስጋት ላይ ሆነው በተለያዩ የእምነት ተቋማት ተደብቀው እንደሚገኙ ለማወቅ ችለናል፡፡ በተማሪዎች ላይ በደረሰው የአካል ጉዳት እና ሕይወት ማለፍ አብን የተሰማውን ጥልቅ ኃዘን ይገልፃል፡፡ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የነገ አገር ተረካቢ ዜጎች ማፍሪያ እንጂ የግጭት ማዕከል መሆን እንደሌለባቸው አብን በፅኑ ያምናል፡፡
በመሆኑም የፌደራል መንግሥቱም ሆነ ዩኒቨርስቲዎች የሚገኙባቸው የክልል መንግስታት በዩኒቨርስቲው ለሚገኙ ተማሪዎች ተገቢ ጥበቃና ከለላ የማድረግ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል፡፡ ከሰሞኑ በአሶሳ ዩኒቨርስቲ ፀብ ባነሳሱና ለግጭቱ ምክንያት በሆኑ አካላት ላይ አፋጣኝ እርምጃ በመውሰድ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በተረጋጋ ሁኔታ እንዲማሩ የሚመለከታቸው አካላት ሕግ የማስከበር ኃላፊነታቸውን በትክክል ሊወጡ እንደሚገባ አብን ያሳስባል፡፡

መሰል የግጭት አዝማሚያዎች በሀሮማያ እና በሌሎችም አንዳንድ ዩኒቨርስቲዎች ስላሉ መንግስት ጉዳት ከመድረሱ በፊት ሕግ የማስከበር እና ለተማሪዎች ጥበቃ የማድረግ ተግባሩን በተገቢው ሁኔታ ሊወጣ እንደሚገባም አብን በአንክሮ ያሳስባል። በተማሪዎች መካከል ግጭት በተነሳ ቁጥር የአማራ ተማሪዎች በተለዬ መልኩ የዘር ተኮር ጥቃት ሰለባ እየሆኑ መሆናቸውን በመረዳት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥትም የዜጎች ደኅንነት የሚጠበቅበትን እና ችግሩ በዘላቂነት የሚፈታበትን መንገድ ማመቻቸት እንደሚገባው እያስገነዘብን የሚመለከታቸው አካላት አማራ ተማሪዎች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ማስቆም የማይችሉ ከሆነ ከሕዝባችን ጋር በመሆን የራሳችንን አማራጭ ለመውሰድ የምንገደድ መሆኑን በጥብቅ እናስጠነቅቃለን። የአማራ ወላጆች በሰላም ወደ ከፍተኛ ትምህርት የላኳቸው ልጆቻቸውን ሬሳ ሲቀበሉ እስከመቼ

Share this post

One thought on “በአሶሳ ዩኒቨርስቲ በተማሪዎች ላይ በደረሰው እና እየደረሰ ባለው ጉዳት ከአብን የተሰጠ መግለጫ- አብን

  1. Meglechaw Tiru neber gin enanet tebaboch ..yemhuran tebaboch edegmewalehu eske meche new ..chnklatachuh ..endezih yeworede mihonew ..lemn yelela biher simot atnagerum dededeboch nachuh !!!

    Reply

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.