በአከራካሪው የ3ሺህ ሜትር መሰናክል ኢትዮጵያ በታሪኳ የመጀመሪያውን ሜዳሊያ አገኘች

Source: https://mereja.com/amharic/v2/154614

BBC Amharic : ኳታር ዶሃ ላይ እየተካሄደ ባለው 17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ላይ በወንዶች የሦስት ሺህ ሜትር የመሰናክል ሩጫ ውድድር ኢትዮጵያዊው ለሜቻ ግርማ ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ አሸነፈ።
ይህ በሦስት ሺህ ሜትር የመሰናክል ውድድር በለሜቻ ግርማ የተገኘው የብር ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ በዘርፉ የመጀመሪያ ሲሆን የተመዘገበው ሰዓትም ለአገሪቱ ክብረ ወሰን ነው ተብሏል።
ለሜቻ ግርማ
ኬንያዊው አትሌት የወርቅ ሜዳሊያውን በወሰደበት በዚህ የመሰናክል ሩጫ ውድድር ላይ ለሜቻ የተቀደመው ከአንድ ሰከንድ በታች በሆነ ጠባብ ልዩነት ነው።
ለሜቻ አንደኛ ሆኖ የወርቅ ሜዳሊያን ካገኘው ኬንያዊው ሯጭ ኮንሴስለስ ኪፕሩቶ ጋር እኩል የመጨረሻውን መስመር በማለፋቸው አሸናፊው ማን እንደሆነ በውድድሩ ማብቂያ ላይ ወዲያውኑ አልታወቀም ነበር።
የውድድሩ ዳኞች በቪዲዮ (ፎቶ ፊኒሽ) ታግዘው ከአንድ ሰከንድ ባነሰ የሰከንዶች ቅንጣት የመጨረሻውን መስመር ኬንያዊው ለሜቻን ቀድሞ እንዳለፈ ከለዩ በኋላ ነው አሸናፊው ሊታወቅ የቻለው።
በስፍራው የሚገኙት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባለስልጣናት ለሜቻ አንደኛ ወጥቷል ብለው አምነው ሰለነበር ይፋ የተደረገውን ውጤት በመቃወም ቅሬታ ለማቅረብ አስበው የነበረ ቢሆንም፤ የመጨረሻውን ሰከንድ የውድድሩን ቪዲዮና ምስሎችን ተመልክተው ካጣሩ በኋላ ቅሬታቸውን ማንሳታቸውን የቢቢሲ ዘጋቢ ገልጿል።
19 ዓመት ሊሆነው ሁለት ወራት የቀሩት ወጣቱ ለሜቻ በዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ መሳተፍ የጀመረው በቅርቡ ሲሆን በኬንያዊያን የበላይነት ስር በነበረው የሦስት ሺህ ሜትር የመሰናክል ውድድር ላይ የብር ሜዳሊያ ያስገኘበት የዶሃው ውድድር ሦስተኛው ዓለም አቀፍ ተሳትፎው ነው።
በውድድሩ አሸናፊ በመሆን የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት የሆነው ኬንያዊው ኮንሴስለስ ኪፕሩቶ በዚህ በፈረንጆች ዓመት

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.