በአክሱም ሀውልት እድሳት ዙሪያ ለመምከር የጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመጪው ሳምንት አዲስ አበባ ይገባሉ

Source: https://fanabc.com/2019/06/%E1%89%A0%E1%8A%A0%E1%8A%AD%E1%88%B1%E1%88%9D-%E1%88%80%E1%8B%8D%E1%88%8D%E1%89%B5-%E1%8A%A5%E1%8B%B5%E1%88%B3%E1%89%B5-%E1%8B%99%E1%88%AA%E1%8B%AB-%E1%88%88%E1%88%98%E1%88%9D%E1%8A%A8%E1%88%AD/

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 4 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) በአክሱም ሀውልት እድሳት ዙሪያ ለመምከር በጣሊያን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሚመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በመጪው ሳምንት አዲስ አበባ እንደሚገባ ተገለፀ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር ከሆኑት አርቱሮ ሉዚ ጋር የአክሱም ሀውልት የእድሳት ስራ ማስጀመር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቻይና ከቤልትና ሮድ ጉባኤ ጎን ለጎን ከጣሊያኑ አቻቸው ጁሴፔ ኮንቴ ጋር በተወያዩበት ወቅት የአክሱም ሐውልትን ለማደሻ የሚውል እርዳታ ከጣሊያን መንግስት ማግኘታቸው የሚታወስ ነው።

እንዲሁም በትናትናው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአክሱም ሀውልት ጉብኝት ማድረጋቸው እና ከአክሱም ከተማ ነዋሪዎች ጋር በተለያዩ ጉዳዩ ላይ ውይይት ማድረጋቸው የሚታወስ ነው።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.