በአዲስ አበባና ዙሪያዋ የሚስተዋለውን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ እየተሰራ ነው

Source: https://fanabc.com/2019/05/%E1%89%A0%E1%8A%A0%E1%8B%B2%E1%88%B5-%E1%8A%A0%E1%89%A0%E1%89%A3%E1%8A%93-%E1%8B%99%E1%88%AA%E1%8B%AB%E1%8B%8B-%E1%8B%A8%E1%88%9A%E1%88%B5%E1%89%B0%E1%8B%8B%E1%88%88%E1%8B%8D%E1%8A%95-%E1%8B%A8/

አዲስ አበባ ግንቦት 16፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ በአዲስ አበባና ዙሪያዋ የሚስተዋለውን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ እየሰራ መሆኑን ገለጸ፡፡

ትራንስፖርት ቢሮው በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ የ9 ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን አቅርቧል።

ቢሮው 248 አዳዲስ የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት መስጫዎችን ወደ ስራ በማስገባት የእቅዱን 65 በመቶ ማሳካቱን ገልጿል፡፡

የቢሮው ሃላፊ ዶክተር ኢንጂነር ሰለሞን ኪዳኔ እስከ ፊታችን ሰኔ ወር ድረስ ተጨማሪያ የብዙሃን ትራንስፖርት መስጫ አውቶቡሶችን ወደ ስራ ለማስገባት እቅድ መያዙን ተናግረዋል፡፡

ለብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት በግንባታ ሂደት ላይ ከሚገኙት የነዳጅ ዴፖዎች መካከል የሸጎሌው 95 በመቶ ግንባታው ተጠናቆ በከፊል አገልግሎት መጀመሩም ተገልጿል፡፡

የቃሊቲና ሰሚት ኮንዶሚኒየም አካባቢ ሁለት ዴፖዎች ግንባታ ደግሞ በቅደም ተከተል 95 በመቶና 65 በመቶ መድረሱም ነው የተገለጸው፡፡

ከዚህ ባለፈም ቢሮው በ9 ወራቱ ከ23 ሺህ በላይ ደንብ በተላለፉ አሽከርካሪዎች ላይ የማስተካከያ እርምጃ መውሰዱን በሪፖርቱ ጠቅሷል።

የቢሮው ሃላፊም ከምክር ቤቱ አባላት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያም ሰጥተዋል።

በሲሳይ ጌትነት

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.