በአዲስ አበባ ከነገ ጀምሮ 560 አውቶብሶች ወደ ስምሪት እንደሚገቡ ተገለጸ

በአዲስ አበባ ከነገ ጀምሮ 560 አውቶብሶች ወደ ስምሪት እንደሚገቡ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማን የትራንስፖርት ችግር ለመቅርፍ ከነገ ጀምሮ 560 የግል ማህበራት አውቶብሶች በኪራይ ወደ ስምሪት አንደሚገቡ ተገልጿል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ከግል የትራንስፖርት ማህበራት ጋር ስምምነት በማድረግ ነው አውቶብሶቹ በኪራይ ወደ ስምሪት አንደሚገቡ የተጠቆመው፡፡
በዛሬው እለትም የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ዣንጥራር አባይን ጨምሮ ሌሎች የከተማዋ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት በመስቀል አደባባይ የስምሪት ፕሮግራሙ ይፋ በመደረግ ላይ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።

The post በአዲስ አበባ ከነገ ጀምሮ 560 አውቶብሶች ወደ ስምሪት እንደሚገቡ ተገለጸ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply