በአዲስ አበባ የሰማያዊ ፓርቲ ወጣት አባላትን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች ታፈሱ

Source: https://kalitipost.com/%E1%89%A0%E1%8A%A0%E1%8B%B2%E1%88%B5-%E1%8A%A0%E1%89%A0%E1%89%A3-%E1%8B%A8%E1%88%B0%E1%88%9B%E1%8B%AB%E1%8B%8A-%E1%8D%93%E1%88%AD%E1%89%B2-%E1%8B%88%E1%8C%A3%E1%89%B5-%E1%8A%A0%E1%89%A3%E1%88%8B/
የፋሲል ከነማና የመቀሌ ከነማ ጨዋታ ከተጠናቀቀ በኋላ በሕዝብ አንድነት የተበሳጨው አገዛዝ የፋሲልን ቡድን ሲደግፉ በነበሩ ወጣቶች ላይ ፖሊሶቹን በማዝመት ድብደባና አፈሳ ፈጽሟል። በቦታው የዓይን ምስክር የነበረ ግለሰብ እንደተናገረው አንድ ሽንት የሚሸናበት ቦታ ጋር እኔን ሲኞር የሚባል ጓደኛዬን ወይንሸት ሞላ አዲሱ ጌታነህን አንድ ይድነቃቸው የሚባል የወይንሸት ጓደኛንና ሌሎች ቢያንስ 20 የምንሆነውን ካስቀመጡ በኋላ በጠረባና በጎማ ዱላ ከደበደቡን በኋላ ወደ አንድ ኮድ 4 አባዱላ መኪና ወሰዱን።
የዓይን ምስክሩ አያይዞም እኔ ከለበስኩት የአፄ ቴዎድሮስ ቲሸርት ላይ ሹራብ ደርቤ ነበር ሌሎች ግን ሁሉም የወልድያንና የፋሲል ከነማን ለብሰው ነበር። ወዳዛ መኪና ማስገባት ሲጀምሩ የሹራቡን ኮፍያ ለብሼ ቀጥ ብዬ ስሄድ ማንም ምንም ሳይለኝ ቀረ። ወዲያው ዘወር ያለ መንገድ አግኝቼ ወደዛ ሄጀ ጓደኛየ ጋር ደወልኩ እሱ በመኪናው ወደ ቤቴ አደረሰኝ። ሌሎቹ ግን ፒያሳ ወዳለ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደዋል። ከእኛ በፊት በመቶዎች የሚቆጠሩ የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች ታፍሰው ተወስደዋል ።
ይህ በ እንዲህ እንዳለ የሰማያዊ ፓርቲ መሪ ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት በፌስቡክ ገጻቸው “ዛሬም የስር ዜና” በሚል ርዕስ
1 አዲሱ ጌታነህ
2 ይድነቃቸው አዲስ
3 ወይንሸት ሞላ
በፋሲል ከነማ እና በመቀሌ ከነማ መካከል የተደረገውን ጨዋታ ተመልክተው ሲመለሱ ተይዘው ጣይቱ ሆቴል ፊት ለፊት በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ታስረዋል” በማለት ተናገረዋል::

Share this post

Post Comment