በአዲስ ዓመት ዋዜማና በበዓሉ እለት በመኖሪያ ቤት በደረሰ የእሳት አደጋ 1ሚሊዮን 50 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት ወደመ

በአዲስ አበባ በአዲስ ዓመት ዋዜማ በአንድ መኖሪያ ቤት በደረሰ የእሳት አደጋ 50 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ አቶ ጉልላት ጌታነህ ለኢዜአ እንደገለጹት ጳጉሜን 5 ቀን 2012 በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 በአንድ መኖሪያ ቤት ላይ ቃጠሎ ተከስቷል።

በቃጠሎው 50 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት የወደመ ቢሆንም በሰዎች ላይ የደረሰ ጉዳት ግን የለም ብለዋል።

በእለቱ ቃጠሎውን በመቆጣጠር ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ማትረፍ መቻሉንም አቶ ጉልላት ገልጸዋል።

መስከረም 1 ቀን 2013 ዓ.ም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 በአንድ የግለሰብ በመኖሪያት ቤት ላይ በደረሰ የእሳት አደጋም አንድ ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን ቡድን መሪው ገልጸዋል።

የእሳት አደጋ ሰራተኞች ባደረጉት ጥረት ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ማዳን መቻሉንም ተናግረዋል።

የተከሰቱትን አደጋዎች ለመቆጣጠር የኮሚሽኑ ሰራተኞች፣ የህብረተሰቡ እና የጸጥታ አካላት ርብርብ ማድረጋቸውን አቶ ጉልላት ገልጸዋል።

በተያያዘ ዜና ጳጉሜን 5 ቀን 2012 በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 የአንድ ግለሰብ መጸዳጃ ቤት ተደርምሶ የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ በሁለት ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ገልጸዋል።

አዉሎ ሚዲያ መስከረም 02/2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply