በአፍጋኒስታን በተፈፀመ ጥቃት የ37 ሰዎች ህይወት አለፈ

Source: https://fanabc.com/2018/09/%E1%89%A0%E1%8A%A0%E1%8D%8D%E1%8C%8B%E1%8A%92%E1%88%B5%E1%89%B3%E1%8A%95-%E1%89%A0%E1%89%B0%E1%8D%88%E1%8D%80%E1%88%98-%E1%8C%A5%E1%89%83%E1%89%B5-%E1%8B%A837-%E1%88%B0%E1%8B%8E%E1%89%BD-%E1%88%85/

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአፍጋኒስታን የተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በምሽት በተፈፀመ ጥቃት የ37 ሰዎች ህይወት ማለፉን የሀገሪቱ መንግስት አስታወቀ።

ታሊባን በሀገሪቱ ፋራህ ግዛት በወሰደው ጥቃት  21 የሀገሪቱ ፓሊስና ብሄራዊ ጦር አባላት መገዳላቸውን ነው መንግስት ያስታወቀው።

ታሊባን በፋራህ የተለያዩ ስፍራዎች በወሰደው ጥቃት የሰዎቹ ህይወት ያለፈ ሲሆን፥ በሌሎች አካባቢዎች በወሰደው ጥቃት ደግሞ የስድስት ሰዎች ህይወት እንዳለፈ ተነግሯል።

በተጨማሪ ከ14 ሰዎች በላይ የአካል ጉዳት እንዳጋጠማቸው የሀገሪቱ መንግስት ይፋ አድርጓል።

በዚህ ወር መጀመሪያ በዚሁ አካባቢ  ታሊባን በፖሊስ የፍተሻ ጣቢያዎች በፈፀመው ጥቃት  የ14 ህይወት እንዳለፈና በስድስት ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት አጋጥሞ ነበር።

ታሊባን በቅርብ ዓመታት  በርካታ የሀገሪቱን ክፍሎች በድንገት መውረሩና የተለያዩ ጥቃቶችን መፈፀሙ መረጃዎች ያመለክታሉ።

በነሃሴ ወር የታሊባን ታጣቂዎች በጋሀዝኒ ከተማ በአምስት ቀናት በወሰደው ጥቃት 150 ሰላማዊ ዜጎች ተገድለዋል።

ምንጭ፥ አልጀዚራ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.