በኢትዮጵያና በኢንዶኔዥያ የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች አደጋ ኩባንያውና ተቆጣጣሪው ባለስልጣን ተጠያቂ ተደረጉ

በኢትዮጵያና በኢንዶኔዥያ የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች አደጋ ኩባንያውና ተቆጣጣሪው ባለስልጣን ተጠያቂ ተደረጉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያና በኢንዶኔዥያ በተከሰከሱት ሁለት ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች አደጋ የአውሮፕላን አምራቹ ቦይንግና የፌደራል አቪዬሽን ባለስልጣን አካላት ተጠያቂ ተደረጉ፡፡

ምርመራውን ለ18 ወራት ሲያካሂድ የቆየው የአሜሪካ ምክርቤት ቦይንግ ቴክኒካል የሆኑ ጉዳዮችን ለማጋራት ዳተኛ ነበር ብሏል፡፡

ምክርቤቱ በግኝቱ ቦይንግ በማክስ ዲዛይንና ልህቀት ላይ ችግር እንደነበረበት በምርመራው ደርሶበታል፡፡

እንዲሁም ተቆጣጣሪ አካል የሆነውን የፌደራል አቪዬሽን ባለስልጣን ጉድለቶቹን ባለመለየቱና የፍቃድ አሰጣጡ ላይ ተጠያቂ አድርጎታል፡፡

በተጨማሪም ኮንግረንሱ የቦይንግ ኩባንያን ነገሮችን ደብቆ የመያዝ ባህሉን ነቅፏል፡፡

የምርመራው ውጤት ይፋ መደረግን ተከትሎ ቦይንግ ስህተት መስራቱን አምኖ 737 ዳግም ወደ ስራ ሊመለስ የሚችልበትን ጉዳይ ላይ እንደሚያተኩር ይፋ አድርገዋል፡፡

እንዲሁም ኩባንያው በሁለቱ አደጋዎች ትምህርት መውሰዱን ቢገልጽም የተጎጂ ቤተሰቦች የቦይንግንና የተቆጣጣሪውን ባለስልጣን መረጃዎችን ይፋ ባለማድረጋቸው እየወቀሱ ይገኛሉ፡፡

በአውሮፓና በአሜሪካ የሚገኙ ተቆጣጣሪዎች በበኩላቸው አንድ የግል ኩባንያ በዘመናዊው ዓለም ውስጥ የገጠመው ትልቁ የደህንነት ቅሌት ነው ብለውታል፡፡

በመጋቢት መጀመሪያ 2011 ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነው ቦይንግ 737 አውሮፕላን 157 ሰዎችን ይዞ ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ በመብረር ላይ ሳለ ቢሾፍቱ አካባቢ ሲደርስ ድንገት መከስከሱ ይታወሳል።

ከዚህ አደጋ ቀደም ብሎ ደግሞ 188 ሰዎችን የያዘው ላየን ኤይር ቦይንግ 737 የተሰኘ የኢንዶኔዢያ የመንገደኞች አውሮፕላን መብረር ከመጀመረ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ መከስሰከሱ የሚታወቅ ነው።

ምክርቤቱ በዚህ ለ346 ሰዎች ህልፈት ኩባንያውንና ተቆጣጣሪውን ተጠያቂ ያደረገበት ሪፖርት 250 ገጸችን መያዙ ተነግሯል፡፡

ምንጭ፦ቢቢሲ

The post በኢትዮጵያና በኢንዶኔዥያ የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች አደጋ ኩባንያውና ተቆጣጣሪው ባለስልጣን ተጠያቂ ተደረጉ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply