በኢትዮጵያ በጉብኝት ላይ ያሉት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ስላለው ሁኔታ ደንገዝገዝ ያለ መልዕክት አስተላለፉ

Source: https://amharic.borkena.com/2018/03/08/%E1%89%A0%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB-%E1%89%A0%E1%8C%89%E1%89%A5%E1%8A%9D%E1%89%B5-%E1%88%8B%E1%8B%AD-%E1%8B%AB%E1%88%89%E1%89%B5-%E1%8B%A8%E1%8A%A0%E1%88%9C%E1%88%AA%E1%8A%AB/

ሬክስ ቲለርሰንሬክስ ቲለርሰን ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር ተገናኝተው በተወያዩበት ጊዜ
ምንጭ: ፋና

ቦርከና
የካቲት 28 2010 ዓ ም

በኢትዮጵያ በጉብኝት ላይ የሚገኙት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሬክስ ቲለርሰን ዛሬ በሃገር ውስጥ ላሉ ጋዜጠኞች ከወርቅነህ ገበየሁ ጋር በመሆን በኢትዮጵያ ስላለው ሁኔታ እንደወትሮው የአሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ አቋም ደንገዝገዝ አስተያየት ለመስጠት ሞክረዋል።

ሁለተኛው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጂ የዛሬ አስራ አምስት ቀን ገደማ እንደታወጀ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ካወጣው “ጠንከር ያለ” በተባለለት መግጫ መነሻነት የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን እንዲያነሳ አጽንኦት ሰጥተው ይናገራሉ ተብሎ ቢጠበቅም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አጠር አርጉት በሚል በለሆሳስ አልፈውታል።

በተጨማሪም “ዲሞክራሲ ሂደት ነው፤ ጊዜ ይወስዳል” በሚል አስተያየት ለ27 ዓመት ስልጣን ላይ የነበረውን ቡድን መታገስ ያስፈልጋል የሚል መልዕክትም አስተላልፈዋል። የአፍቃሪ ህወሓት ተሟጋቾች እና ደጋፊዎች መጀመሪያ ሬክስ ቲለርሰን ነገር ሊያመጡ ይችላሉ የሚል ስጋት የነበራቸው ቢሆንም ፤ የዛሬውን ንግግራቸውን ከሰሙ በኋላ እፎይታ እንደተሰማቸው በማህበራዊ ድረ ገጽ ከሚያስተጋቧቸው መልዕክቶች መረዳት ይቻላል።

ሬክስ ቲለርሰን ከወርቅነህ ገበየሁ በተጨማሪም ስልጣን ለመልቀቅ ከጠየቁት ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋርም ተገናኝተው ተነጋግረዋል።

በተመሳሳይ ዜና ስመጥሩ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ሰርጌ ላቭሮቭ ለኦፊሲየላዊ ጉብኝት ዛሬ ኢትዮጵያ ገብተዋል። ጉብኝታቸው የመቶ ሃያ ዓመት እድሜ ባለው የኢትዮጵያ እና የሩሲያ ግንኙነት ላይ ያተኩራል ተብሏል። ሩሲያ ከኢትዮጵያ ጋር በትምህርት ፤ በግብርና እና በጤና ትብብር ከማግረግ በተጨማሪም የኒኩሊየት ኃይል ማመንጫ ለመገንባትም ፍላጎት እንዳላት እየተነገረ ነው።
__
ወቅታዊ መረጃን ለማግኘት ቦርከናን በፌስ ቡክ ላይክ ያድርጉ።

Share this post

One thought on “በኢትዮጵያ በጉብኝት ላይ ያሉት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ስላለው ሁኔታ ደንገዝገዝ ያለ መልዕክት አስተላለፉ

  1. Tilerson’s cheap talk in in Ethiopia’s capital today clearly demonstrates that Ethiopians have no option to die for their cause and provide freedom for the next generation.

    Reply

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.