በኢትዮጵያ በፕሪምየር ሊግ የአራተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ተካሂደዋል

Source: https://fanabc.com/2018/12/%E1%89%A0%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB-%E1%89%A0%E1%8D%95%E1%88%AA%E1%88%9D%E1%8B%A8%E1%88%AD-%E1%88%8A%E1%8C%8D-%E1%8B%A8%E1%8A%A0%E1%88%AB%E1%89%B0%E1%8A%9B-%E1%88%B3%E1%88%9D/

አዲስ አበባ፣ ህዳር 23፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በዛሬው ዕለት በክልል ከተሞችና በአዲስ አበባ  ጨዋታዎች አስተናግዷል።

በርካታ ተመልካቾችን ያስተናገገደው የፋሲል ከነማና  የኢትዮጵያ ቡና ጨዋታ 0 ለ 0 በሆነ ውጤት ተጠናቋል።

አዳማ ከተማ ከሲዳማ ቡና ያደረጉት ሌላኛው ጨዋታ 1 ለ 1 አቻው ውጤት ነው የተጠናቀቀው።

በጨዋታው ለባለሜዳዎቹ ዳዋ ሁቴሳ በ37ኛው ደቂቃ ሲያስቆጥር የሲዳማ ቡናን የአቻነት ግብ አዲስ ግደይ ማስቆጠር ችሏል።

ወላይታ ድቻ መቐለ 70 እንደርታን አስተናግዶ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት እንግዳውን ቡድን ማሸነፍ ችሏል።

ወላይታ ወሳኝ ሶስት እንዲያገኝ ያስቻለችውን ግብ ፀጋዬ አበራ በ82ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል።

በሌላ ጨዋታ ባህር ዳር ከተማ ሀዋሳ ከተማን አስተናግዶ ያለምንም ግብ 0 ለ 0 በሆነ ውጤት ተላያይተዋል።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.