በኢትዮጵያ እየተፈጸመ ያለው የሙስና ወንጀል መጠን እየጨምረና ወንጀሉ የሚፈጸምበት ረቂቅነትም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተራቀቀ መምጣቱ ተነገረ።

Source: https://mereja.com/amharic/v2/189409

BBC Amharic : የኢትዮጵያ የሥነ-ምግባር እና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አየልኝ ሙሉዓለም ለቢቢሲ እንደተናገሩት የሙስና ወንጀል በአገር ላይ እያስከተለ ያለውን ኪሳራ ለመከላከል የተደራጀ እና ንቃተ ህሊናው ከፍ ያለ ማኅብረሰብ ለመፍጠር እንዲሁም ጥፋተኞችን ተጠያቂ ለማድረግ፤ የሥነ-ምግባር እና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን፣ ፖሊስ እንዲሁም አቃቤ ሕግ በጥምረት ከመቼውም በላይ እየሰሩ ይገኛሉ ብለዋል።
ከለውጡ ጋር ተያይዞ የጸረ-ሙስና ኮሚሽን ከመቼውም በላይ የተነቃቃበት እና የተለወጠበት ደረጃ ላይ ነው የሚገኘው የሚሉት ኮሚሽነሩ፤ እርሳቸው የሚመሩት ኮሚሽን ግን ከዚህ ቀደም የነበረውን አይነት ተጽእኖ መፍጠር እንደማይችል ይስማማሉ።
የኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም የነበሩት ኃላፊነቶች እንዲቀሩ መደረጉ የነበረውን ተደማጭነት እና ተጽዕኖ ፈጣሪነትን እንዳሳጣው ኮሚሽነሩ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
የሥነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አየልኝ ሙሉዓለምኮሚሽኑ ከፖሊስ እና ከአቃቢ ሕግ ጋር በቅርበት ስለሚሰራ እንደተቋም ተዳክሟል ማለት አይቻልም የሚሉት ኮሚሽነር አየልኝ፤ “ወደፊት ግን ሥነ-ምግባር እና ጸረ-ሙስና ተብሎ እስከተቋቋመ ድረስ ያለ ምርመራ ጠንካራ ሆኖ ለኅብረተሰቡ ችግር ምላሽ መስጠት የሚችል አይሆንም” ብለዋል።
ጸረ ሙስና ኮሚሽን ቀደም ሲል ሙስናን የመከላከል፣ የሙስና ወንጀል የመመርመርና ሕግ የማስከበር ኃላፊነቶች እንደነበሩት አስታውሰው፤ አሁን ግን ለሙሰና ተጋላጭ የሚያደርጉ አሰራሮችን ማሻሻል፣ ተቋማትን ማጠናከር እና መደገፍ፣ እንዲሁም ሙስናን የሚጠየፍ ኅብረተሰብ ለመፍጠር ትኩረት አድርጎ እየሰራ እንደሚገኝ ለቢቢሲ አስረድተዋል።
ጸረ-ሙስናን የሚያጠናክር እና አቅም እንዲኖረው የሚያስችል አሠራር ቢዘረጋ መልካም ነው የሚሉት ኮሚሽነሩ፤ “ሙስና የሚፈጸምባቸው የወንጀል አይነቶች እየተራቀቁ እንደመምጣታቸው ወንጀሉን የመከላከል እና የመመርመር ሥራው ተጣምሮ አቅሙ ባላቸው ብቁ ሠራተኞች ቢከናወን ውጤታማ መሆን ይቻላል” ሲሉም ይጠቁማሉ።
ኮሚሽነሩ 2007 እና

Share this post

One thought on “በኢትዮጵያ እየተፈጸመ ያለው የሙስና ወንጀል መጠን እየጨምረና ወንጀሉ የሚፈጸምበት ረቂቅነትም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተራቀቀ መምጣቱ ተነገረ።

  1. በጎሳ ፖለቲካ መሰረት ላይ በተደራጀና አፖርታይድን በሚያራምድ የፖለቲካ ሥርዓት ውስጥ ሙስናን እናጠፋለን ወይም እንዋጋለን ማለት ትርጉም የለውም። በመጀመሪያ ትላንት ትግሬዎችን፣ ዛሬ ደግሞ ኦሮሞዎችን ምርጥ ህዝብ ያደረገው የፋሽስት/የናዚ መንግስታዊ ሥርዓት ሙሉ በሙሉ ፈርሶ የቡድንን ሳይሆን የግለሰብን መብት የህገመንግስቱ ዋነኛ መሰረት ያደረገ የህግና የዲሞክራሲ ሥርዓት መምጣት ይኖርበታል።

    Reply

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.