በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የሚደርሰዉ የመጣዉን የቡድን ጥቃትና አመፅን መንግሥት ሊያስቆም ይገባል – «አምነስቲ ኢንተርናሽናል»

Source: https://mereja.com/amharic/v2/53694

ጥላቻ አዘል መልክቶች ቁጥጥር ሊደረግባቸዉ ይገባል በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የሚደርሰዉ የመጣዉን የቡድን ጥቃትና አመፅን መንግሥት ሊያስቆም ይገባል ሲል ዓለምአቀፉ የየሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት «አምነስቲ ኢንተርናሽናል» ገለፀ። በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ከአገር ዉጭ የሚሰራጭ ማንኛዉም የጥላቻ መልክት በዓለምአቀፍ ደረጃ ወደ ሕግ ማምጣት እንደሚቻልም አያይዞ ጠቅሶአል።
በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የሚታየዉን የቡድን ጥቃትና አመፅን መንግሥት ሊያስቆም ይገባል ሲል ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት «አምነስቲ ኢንተርናሽናል» ገለፀ። የአምስንቲ ኢንተርናሽናል የሠብአዊ መብት አጥኚ ዛሬ ለ«DW» እንደተናገሩት፤ ሰዎች መብታቸዉን አልፈዉ የሰዉን መብትን በሚነኩበት ጊዜ መንግሥት ርምጃ ካልወሰደ ከሆደ ሰፊነት አልፎ ግዴታዉን አለመወጣም። በተለይ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ከአገር ዉስጥም ሆነ ከዉጭ የሚሰራጩ ጥላቻ አዘል መልክቶችን መንግስት ሊቆጣጠራቸዉ ይገባል

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.