በኢትዮጵያ የትግራይ የበላይነት እና ተጠቃሚነት ግልፅና ተጨባጭ ማስረጃ

Source: http://welkait.com/?p=11998
Print Friendly, PDF & Email

ከአማራና ኦሮሞ ትብብር ይለምልም ፕሮጀክት (አኦትይፕ)

ከዚህ በታች የቀረበው ሰንጠረዥ ከኢትዮጵያ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ የተገኘ መረጃ ሲሆን። ይህ መረጃ እኤአ በ2014 በኤሮፓን ጆርናል ኦፍ ቢዝነስ ኤንድ ማኔጅመንት በሆነ ጆርናል ላይ ከታተመ የምርምር ፅሁፍ የተገኛ ነው። ይህ መረጃ በኢትዮጵያ መንግስት በይፋ የወጣና በአለም አቀፍ ተቋማትም የተረጋገጠ ነው። ይህ መረጃ ወያኔዎች በግልፅ ያመኑት ሲሆን ሌላ የሚደበቁትና የሚያጭበረብሩት ብዙ መረጃ እንዳለ ደግሞ ግምት ውስጥ መግባት ይገባዋል። ወያኔዎች ባመኑት መረጃ ይህን የሚያህል ለትግራይ አድሎና የትግራይ የበላይነት ካለ በተደበቁት መረጃዎች ውስጥ የእጥፍ እጥፍ አድሎና የበላይነት እንዳለ መገመት ቀላል አይደለም። መረጃው የሚያመለክተው ኢትዮጵያ ውስጥ እኤአ ከ1996 እስከ 2009 ድረስ በሰራ ሶስት ዓመታት ውስጥ ስለተመሰረቱት እንዱስትሪዎች የተመለከተ ነው። በዚህ መረጃ መሰረት በአገሪቱ ውስጥ በ2009 የተመዘገቡት ኢንደስትሪዎች 40 ፐርሰንቱ የሚገኙት በአዲስ አበባ፣ 9 ፐርሰንት በትግራይ ክልል፣ 10 ፐርሰንት በአማራ፣ 20 ፐርሰንት በኦሮሚያ፣ 13 ፐርሰንት በደቡብ፣ 0.6 ፐርሰንት በአፋር፣ 0.6 ፐርሰንት በሶማሌ፣ 0.1 ፐርሰንት በቤንሻንጎል፣ 0.1 ፐርሰንት በጋምቤላ፣ 1.2 ፐርሰንት በሐረር፣ 2 ፐርሰንት በድሬዳዋ ነው። ይህ መረጃ እንደሚያመለክተው የትግራይ ክልል ከአገሪቱ የሕዝብ መጠን 5 በመቶ በሚገመት የሚኖርበት ክልል የኢንዱስትሪ ባለቤት ድርሻው ግን 9 መቶ ይደርሳል ማለት ነው። ይህ ማለት የትግራይ ክልል መሆን ከሚገባው አንፃር በእጥፍ በሚጠጋ መቶ ፐርሰንት ሲበልጥ፤ በአንፃሩ ከአገሪቱ የሕዝብ መጠን ወደ 30 በመቶ በሚገመት የሚኖርበት የአማራ ክልል የኢንዱስትሪ ድርሻው 10 በመቶኛ ሲሆን ይህም መሆን ከሚገባው አንፃር በሁለት እጥፍ ማለትም በሁለት መቶ ፐርሰንት ያነሰ ነው። ….  (Read more, pdf- Tigray Domination of Ethiopia with Good Evidences )

(Read more, pdf- Tigray Domination of Ethiopia with Good Evidences )

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.