በኢትዮጵያ የፈረጠመ የኃይል መዳፍ ውስጥ የቀጠናው የትብብር ኮረንቲ ያንጸባርቃል – ፀደቀ ወልደ

ሕዳሴ ግድቡን አስመልክቶ የከረሩ ሙግቶች ሊካሄዱ የሚችሉባቸው በርካታ አማራጮች ይኖራሉ፤ ‹ጉልህ ጉዳት ምንድን ነው› ከሚለው ሙግት አንስቶ ‹አወያዮች ወይስ እጅ ጠምዛዦች› እስከሚለው ውንጀላ ድረስ፣ ወይም ደግሞ በገራገሩ ግን የዋህነት በሚስተዋልበቱ የናይል ተፋሰስ ሀገራትን የ“ትብብር ማዕቀፍ ስምምነት” (Cooperative Framework Agreement ወይም Undugu) መንፈሱን አስጠብቆ ውይይቱን የማስቀጠል ፍላጎት፣ ከዚያም አልፎ ‹‹በ2015 የተወሰነውን ‹ዲክላሬሽን ኦፍ ፕሪንሲፕልስ› ልንከተል ይገባል›› እስከሚለው ነባራዊ ሁኔታን  ያገናዘበ ውትወታ ድረስ፤  እነዚህ ሁሉ ለጽሁፍ የሚመቹ አማራጮች ናቸው፡፡   የጉዳይ ምርጫዎቹ ይብዙ እንጂ፣ በአባይ ተፋሰስ ዙሪያ የተራዘመ ቀውስ ምን ሊያስከትል እንደሚችል ግምት ውስጥ በማስገባት፣ ይህ ጽሁፍ በሚከተሉት ሶስት ጉዳዮች ላይ ያተኩራል፤ የሕዳሴ ግድቡ ኢትዮጵያን በወንዝ ለተጋመደቻቸው ወገኖቿ የክፉ ቀን መከታ እንደሚያደርጋት

Source: Link to the Post

Leave a Reply