በኢትዮጵያ 2 ሚሊዮን የሚጠጉ  ሰዎች በአገር ውስጥ መፈናቅላቸው ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ      መስከረም 6 ቀን 2013 ዓ.ም          አዲስ አበባ ሸዋ ዓለም አቀፉ የስደ…

በኢትዮጵያ 2 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በአገር ውስጥ መፈናቅላቸው ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መስከረም 6 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ዓለም አቀፉ የስደ…

በኢትዮጵያ 2 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በአገር ውስጥ መፈናቅላቸው ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መስከረም 6 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ሰሞኑን ይፋ ባደረገው ዘገባ በኢትዮጵያ 1.8 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች በአገር ውስጥ ተፈናቃይ መሆናቸውን አመልክቷል። ድርጅቱ መረጃውን ለማሰባሰብ ከ1200 በላይ ተፈናቃዮች በሚገኙባቸው ጊዜያዊ ጣቢያዎችና በ1200 መንደሮች ላይ የመስክ ዳሰሳ ማድረጉን አመልክቷል። ዘገባው ከሰኔ እስከ ሀምሌ ወር ያለውን ጊዜ የሚያሳይ ሲሆን፤ተጠናቆ ይፋ የሆነው ግን በተያዘው መስከረም ወር ነው። መረጃው በመንግስት ባለስልጣናት ዘንድ ተቀባይነት ያለው መሆኑንም ድርጅቱ ገልጿል። በመንገድ ተደራሽነት እና ከአየር ንብረት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች የተነሳ የክልሎች ምዘና ሊለያይ ቢችልም አፋርን ፣ አማራን ፣ ትግራይን፣ቤኒሻንጉል ጉሙዝን፣ ድሬደዋን ፣ ጋምቤላን ፣ ሀረሪን ፣ ኦሮሚያን ፣ ሲዳማን ፣ ደቡብንና ሶማሌ ክልሎችን ጥናቱ ለመዳሰስ ሞክሯል። በጥናቱ መሰረትም ከጠቅላላው 1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ውስጥ በደቡብና በአዲሱ ሲዳማ ክልል በድምሩ 93,982 ሰዎች ተፈናቅለዋል። ከነዚህም ውስጥ 66,994 ተፈናቃዮች (71%) በግጭቶች የተፈናቀሉ ሲሆን፤ 26,988 ተፈናቃዮች (29%) በደረሰ የጎርፍ አደጋ ተፈናቅለዋል ሲል ድርጅቱ አመልክቷል ሲል ተስፋ ኢትዮጵያ በቴሌግራም ገጹ አስፍሯል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply