በኢየሩሳሌም ጎለጎታ የሃይማኖት አባቶች ተደበደቡ

Source: https://amharic.ethsat.com/%E1%89%A0%E1%8A%A2%E1%8B%A8%E1%88%A9%E1%88%B3%E1%88%8C%E1%88%9D-%E1%8C%8E%E1%88%88%E1%8C%8E%E1%89%B3-%E1%8B%A8%E1%88%83%E1%8B%AD%E1%88%9B%E1%8A%96%E1%89%B5-%E1%8A%A0%E1%89%A3%E1%89%B6%E1%89%BD/

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 9/2011) በኢየሩሳሌም ጎለጎታ ግቢ ውስጥበሃይማኖት አባቶች ላይ ድብደባ መፈጸሙ ተገለጸ።

በቤተክርስቲያኒቱ ቅጥር ግቢ በሚካሄድ
ስብስባ ላይ በተፈጠረ አለመግባባት አባቶቹ ላይ ከፍተኛ የሆነ ድብደባ መፈጸሙን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።

የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳዳሪ ብጹእ
አቡነ እምባቆምን ጨምሮ ሶስት አባቶች በተፈጸመባቸው ድብደባ ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑ ታውቋል።

ድብደባውን የፈጸሙት የህወሀት
ደጋፊ የሆኑ ሶስት የቤተክርስቲያኒቱ አባቶች ሲሆኑ በእስራዔል ፖሊስ ቁጥጥር ስር ሆነው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን የደረሰን
መረጃ አመልክቷል።

በእስራዔል የኢትዮጵያ አምባሳደር
አቶ ጸጋዬ በርሄ ከቴላቪቭ ወደ ኢየሩሳሌም ገብተው በጉዳዩ ዙሪያ ስብሰባ መቀመጣቸው ተገልጿል።

The post በኢየሩሳሌም ጎለጎታ የሃይማኖት አባቶች ተደበደቡ appeared first on ESAT Amharic.

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.