በእስር ላይ ያሉ የባልደራስ ፕሬዝዳንት አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ በ7 ተከሳሾች ላይ አቃቤ ህግ ክስ መመስረቱ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ      ጳጉሜ 5 ቀን 2012 ዓ.ም…

በእስር ላይ ያሉ የባልደራስ ፕሬዝዳንት አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ በ7 ተከሳሾች ላይ አቃቤ ህግ ክስ መመስረቱ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጳጉሜ 5 ቀን 2012 ዓ.ም…

በእስር ላይ ያሉ የባልደራስ ፕሬዝዳንት አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ በ7 ተከሳሾች ላይ አቃቤ ህግ ክስ መመስረቱ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጳጉሜ 5 ቀን 2012 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከአቶ እስክንድር ነጋ እስከ 3ኛ ያሉ ተጠርጣሪዎች ላይ በሽብር ወንጀል፣ ቀሪዎቹን ከ4ኛ እስከ 7ኛ ተከሳሾች ላይ ደግሞ የእርስ በእርስ ግጭት በመፍጠር ወንጀል ሲል አቃቢ ህግ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ መመስረቱ ተነግሯል። እነ እስክንድር ነጋ አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያን ተከትሎ በአዲስ አበባ ከተማ ከደረሰው የሰው እና ንብረት ጉዳት ጋር በተያያዘ ተጠርጥረዋል በሚል በእስር ላይ መሆናቸው ይታወቃል። በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ እንደ ማንኛውም ሰው በሚዲያ ከመስማቴ ውጭ ቀድሞ የተነገረን ነገር የለም ያሉ ሲሆን እነ እስክንድር ነጋ ዛሬ ጳጉሜ 5 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት ላይ ቀጠሮ እንዳላቸው ነበር የምናውቀው ብለዋል። ነገር ግን ጠዋት ላይ ድንገት ወደ ልደታ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመውሰድ የሽብር እና የእርስ በርስ ግጭት ክስ እንደተመሰረተባቸው ሰምተናል ነው ያሉት። በመዝገቡ ተራ ቁጥር መሰረት 1 እስከ 3 ያሉት እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮልና ቀለብ ስዩም በሽብር የተከሰሱ ሲሆን ከተራ ቁጥር 4 እስከ 7 ያሉት በእርስ በርስ ግጭት ክስ እንደተመሰረተባቸው ለማወቅ ተችሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply