“በእጅ የያዙት ወርቅ መዳብ ሆኖብን ነው እንጂ፤ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን የመሰለ ነገር የለም” – ሲራክ አስፋው

Source: https://tracking.feedpress.it/link/17593/13437783
https://tracking.feedpress.it/link/17593/13437784/amharic_92ae2e12-9c86-4c0d-ba9b-42116829a63c.mp3

አቶ ሲራክ አስፋው፤ የኔዘርላንድስ ነዋሪ ኢትዮጵያዊ ናቸው። የ18ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ ዘውድ ድንገት ቤታቸው እንደምን ገብቶ እንዳይወጣ አድርገዋል። ዘውዱንም ለ21 ዓመታት ደብቀው አቆይተው ወደ ታሪካዊ ሥፍራው ጨለቆት ቤተክርስቲያን በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በኩል እንዲደርስ በማድረጋቸውና ከ41 ዓመታት የስደት ሕይወት በኋላ አገራቸውንና ሕዝባቸውን በማየታቸው ስላደረባቸው ገደብ የለሽ ሐሴት ይናገራሉ።

Share this post

One thought on ““በእጅ የያዙት ወርቅ መዳብ ሆኖብን ነው እንጂ፤ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን የመሰለ ነገር የለም” – ሲራክ አስፋው

 1. በመጀመሪያ ከአገር ቤት ተሰርቆ ሲወጣ ከጅቡቲ አግኝቼ ገዛሁት ያሉን አቶ ሰይድ የነገሩን የተለየ ነው ፤ በአደራ እንዲያስቀምጥ ለአቶ ሲራክ ሰጠሁት ነው ያሉን እናንተ ደግሞ ድንገት እቤታቸው ገባ ነው የምትሉን ፡ እዚህ ለሆላንድ ሜድያ አቶ ሲራክ የተናገሩት (በሚዲያ እንደሰማነው) ፍጽም የተለየ እውነት የማይመስል ታሪክ ነው። ለሁሉም አቶ ሲራክ ያልነገሩን ብዙ ጉዳይ አለው።
  ዋናው ጉዳይ ለምን በአደራ የተሰጣቸውን እቃ በሙሉ አልመለሱም? ዋንጫዎች ስኒ የመሰሉም አሉ ተብሎ ነብር ? ለ21 አመት ድብቀው አኑረውት አሁን ወደ ታሪካዊው ቦታ መለሱት ተብሏል ፤ እዚህ በሆላንድ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ የሚለውና ዘውዱን ገዛሁት የሚሉት አቶ ሰይድ የሚናገሩት የተለየ ነው፡ እኔ የሚመስለኝ መሸጥ ሲያቅታቸው የመለሱት ይሆናል አለዚያም አቶ ሲራክ የእርጅ ጊዜያቸውን ከአብይ መንግስት ጋር ሊሞዳሞዱ በመፈለግ የድሮ የጥቅም አጋራቸውን አቶ ሰይድን ለእርድ ማቀረባቸው ሊሆን ይችላል።
  እኔ ግን ይህን አስተያየት ለመጻፍ ያበቃኝ የዘራፊ ተባባሪን ፤ ውሸታምን የተለየ ክቡር ሥም እየሰጡ ማሞካሸት አስገርሞኝ ነው።
  በአሁኑ ጊዜ በእኛ አገር የተለመደው ታስሮ የተፈታን ጀግና ! አንድ ስብሰባ ላይ የተናገረ ለህዝብ አሳቢ ! ነጻ አውጭ እየተደረገ ማስመሰልና ያልተገባ ቦታ መስጠት ምን ያህል አደገኛ መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል ። ለዚህ ጥሩ ምሳሌ መራራ ጉዲና የሆነውን ማየት ነው !! ሌባን ሌባ ውሸታምን ውሽታም ማለት ያስፈልጋል፤ ይህንን በግዜው ስላላልን ስላልተናገርን ነው የተረት ታሪክ አገራችንን እያፈረሰ ያለው።
  ጎበዝ ቡና አብረን ስለጠጣን ወይም በስደት አብረን ስለኖርን ለስህተትና ክደት ትብብር ማድረግ አይገባንም። ለዚህ ወራዳ ሥራ ምንም ይሉኝታ የለኝም
  መስፍን

  Reply

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.