በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሮ ወለጋ ዞን በአሙሩ፣በጃርቴ እና በደዱ ወረዳዎች የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች የሚፈፅሙት አማራ ተኮር ጥቃት እንደቀጠለ መሆኑ ተነገረ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   ጥቅምት…

በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሮ ወለጋ ዞን በአሙሩ፣በጃርቴ እና በደዱ ወረዳዎች የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች የሚፈፅሙት አማራ ተኮር ጥቃት እንደቀጠለ መሆኑ ተነገረ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት…

በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሮ ወለጋ ዞን በአሙሩ፣በጃርቴ እና በደዱ ወረዳዎች የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች የሚፈፅሙት አማራ ተኮር ጥቃት እንደቀጠለ መሆኑ ተነገረ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 6 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ሁለት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ አቶ ኢሳ አደምን፣ተስፋሁን አላምኔን፣ሞላ አህመድን፣አድማሱ የሱፍንና ሌሎች በርካታ በአካባቢው ነዋሪ የሆኑ ንፁሀን አማራዎችን በግፍ የገደለው የኦነግ ሸኔ ጦር አሁንም በእኩይ ተግባሩ እንደቀጠለ መሆኑ ተነግሯል። ጥቅምት 5 ለ6 ሌሊት ላይም በአሙሩ ወረዳ ሲደን ቀበሌ ያቀናው የኦነግ ሸኔ ጦር አቶ የኔአለም አየለ የተባለ አማራን በጥይት ገድሏል። የኦሮሚያ ክልል የልዩ ሀይል አባላትም በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ እየወሰደ አይደለም፤ መረጃ በመለዋወጥ አብረው እየሰሩ እስኪመስል ድረስ ንፁሀንን ገድለው፣ጦር መሳሪያና ሌሎች ንብረት ዘርፈው ሲሄዱ ማንም ለመከላከል ጥረት ሲያደርግ እየተስተዋለ አይደለም ብለዋል። የኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይልም ትናንት አቶ ስሜነህ አታላይ እና አቶ ገዳሙ ዋለ የተባሉ በምስራቅ ወለጋ ዞን የኪረሞ ወረዳ ነዋሪ የሆኑ አማራዎችንም የጦር መሳሪያ አላችሁ በሚል ሽፋን እየተሳለሙ ከነበሩበት ቤተ ክርስቲያን በሀይል በማስወጣት አስሮ ስለመውሰዱ የተናገሩት ነዋሪዎቹ ይህም የኦነግ ሸኔ ጦር በንፁሀን ላይ ከሚያደርሰው በደል ያልተናነሰ ነው ብለዋል። በተመሳሳይ ጥቅምት 5 ቀን 2013 ዓ.ም በአሙሩ ወረዳ በሲደን ቀበሌ አንድ በጎችን የሚጠብቅ ልጅም በታጣቂዎች ታግቶ ወደ ጫካ የተወሰደ ሲሆን እስካሁን አድራሻው አልታወቀም ሲሉ ተናግረዋል። ሀዘን ላይ ያሉትን የአቶ የኔአለም አየለ ባለቤትን ወ/ሮ መንበረ አደመ እንዳነጋገርነው ከምሽቱ 4 ሰዓት አካባቢ የመጡ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ቦንብ ጥለዋል፤ በጥይት ባለቤታቸውን የገደሉ ሲሆን ልጃቸውን ይታያል የኔአለም ግንባሩ ላይ በጥይት አቁስለውት ለህክምና እርዳታ መወሰዱን ተናግረዋል። የ9 ልጆች አባት አቶ የኔአለም አየለ በአሙሩ ወረዳ ሲደን ቀበሌ ለዘመናት ይኖሩ እንደነበር የተናገሩት ወ/ሮ መንበረ የጦር መሳሪያ እንዳልነበራቸው ገልፀዋል። ስርዓተ ቀብሩ ዛሬ ጥቅምት 6 ቀን 2013 ዓ.ም በሲደን ቀበሌ በማርያም ቤተ ክርስቲያን እንደሚፈፀም አስታውቀዋል። በተያያዘ በጃርቴ ወረዳ ሀሮዳይ ቀበሌም የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በአርሶ አደሩ ላይ ድንገት በከፈቱት ተኩስ በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሀን በጫካ በተበታትነዋል፤ ይሙቱ ይኑሩ የምናውቀው ነገር የለም ያሉት ሌላኛው ምንጫችን ድርጊቱ የተፈፀመው ጥቅምት 4 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 6 ሰዓት ላይ መሆኑን አስታውቀዋል። ዙሪያውን መትረጊዬስ በማጥመድ ከአስር በላይ የጦር መሳሪያ መግፈፋቸውን የተናገሩት ነዋሪዎች ከአርሶ አደሮቹ በተሰጠው የአጸፋ ተኩስም አንድ የኦነግ ሸኔ ታጣቂ ሲገደል፣ ሌላ አንድ ታጣቂ ደግሞ መቁሰሉን ጠቁመዋል። አሁንም በአካባቢው ከክልሉ ልዩ ሀይል ይልቅ የመከላከያ ሰራዊት ገብቶ እንዲያረጋጋና የኦሮሚያ ክልል መንግስትም የዜጎችን ሰላምና ደህንነት እንዲያስከብር ጠይቀዋል። ስማቸውን ለመናገር ያልፈለጉት የአሙሩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪም ስብሰባ ላይ ነኝ በማለት በንፁሀን ላይ በተደጋጋሚ እየተፈፀመ ስላለው ግድያ፣እገታና ዝርፊያ መረጃ ለመስጠት አልፈቀዱም። ኦነግ ሸኔ በሆሮ ጉድሮ ወለጋ ዞን ጃርቴና አሙሩ ወረዳዎች፣በደዱ ወረዳ ፊንጭ ውሀ ስኳር ፋብሪካና በመተሀራ አካባቢ ዘርና ሀይማኖት ቆጥሮ መግደል፣መድፈር፣መዝረፍና ማፈናቀል መደበኛ ስራው ከሆነ ቆይቷል። ለዚህ የኦነግ የጭካኔ ጥግ ማሳያም በግፍ ከደርዘን በላይ ተገድለውበት የሀዘን ካባና ማቅ የለበሰውን በምስራቅ ጎጃም የባሶ ሊበን ወረዳ አማራን መጥቀስ በቂ ነው። ከአካባቢው ነዋሪዎችና ከሟች አቶ የኔአለም አየለ ባለቤት ከወ/ሮ መንበረ አደመ ጋር ያደረግነውን ቆይታ በአማራ ሚዲያ ማዕከል የዩቱብ አድራሻ ይጠብቁ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply