በኦሮሚያ ክልል መተሀራ አካባቢ ከቆጋ ግድብ በተለቀቀው ከፍተኛ ውሀ ምክንያት የተፈናቀሉ ወገኖች “በቂ እርዳታ እየደረሰን አይደለም” ሲሉ ቅሬታ አቀረቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መስከረም…

በኦሮሚያ ክልል መተሀራ አካባቢ ከቆጋ ግድብ በተለቀቀው ከፍተኛ ውሀ ምክንያት የተፈናቀሉ ወገኖች “በቂ እርዳታ እየደረሰን አይደለም” ሲሉ ቅሬታ አቀረቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መስከረም 10 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በኦሮሚያ ክልል ከቆጋ ግድብ የተለቀቀው ከፍተኛ ውሀ በሽህ የሚቆጠሩ የመተሀራ አዲስ ከተማ 01 ቀበሌና የገልቻ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ነዋሪዎችን እንዲፈናቀሉ አድርጓል ያሉት ተፈናቃዮች በቂ እርዳታ እየተደረገልን አይደለም ሲሉ ቅሬታቸውን ለአማራ ሚዲያ ማዕከል አቅርበዋል። ነሀሴ 27 ቀን 2012 ዓ.ም የተፈናቀሉት በሽህ የሚቆጠሩ ወገኖች መሆናቸውን የጠቀሱት የአካባቢው ነዋሪ አብዛኞች ወደየዘመድ አዝማዱ መበታተናቸውንና በመጠለያ ውስጥ ላሉትም የሚሰጠው እርዳታ በቂ ካለመሆኑም በላይ አድሎአዊ አሰራር እየታየበት መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል። በመተሀራ ስኳር ፋብሪካ አካባቢ በፈንታሌ ወረዳ ጎዲኖ ት/ቤት አካባቢ አያሌ ተፈናቃዮች ተጠልለው እንደሚገኙ የተናገሩት ምንጫችን ከሳምንት በፊት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንና ቀይ መስቀል የተላከ እርዳታ ነው በሚል ለተወሰኑ ተጎጅዎች መሰጠቱን አስታውቀዋል። ይሁንና እርዳታው ላልተፈናቀሉ አንዳንድ ሰዎች ጭምር ተላልፎ የመሰጠትና በሌሊት እየተጫነ የሚወጣበት ሁኔታ መስተዋሉን የተናገሩት ተጎጅው “ልክ አይደለም፣ ስለምን በጨለማ እና በድብቅ ከመጋዝን ተጭኖ ይወጣል” ያሉ ሰዎችም እስከመደብደብ መድረሳቸውን ገልፀዋል። በተያያዘም በቂ እርዳታ እየደረሰን አይደለም በሚል ከአስር ቀን በፊት ለጉብኝት ለመጡት ለሰላም ሚኒስትሯ ለወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ቅሬታ ያቀረቡ ሁለት ግለሰቦችም ትናንት መስከረም 9 ቀን 2013 ዓ.ም ምሽት ላይ በፖሊስ ስለወሰዳቸው አክለው ተናግረዋል። ለበዓል ይሰጣል በሚል እንድንመዘገብ ቢደረግም ለተወሰኑት ከተሰጠ በኋላ አልቋል በመባሉን የጠቀሱት ተጎጅ እንደአብነትም አምስት ቤተሰብ ያላቸው ተፈናቃይ 25 ኪሎ ግራም ሩዝ እና አንድ ሸራ ብቻ እንደደረሳቸውና ሌሎችም ተመሳሳይ ችግር እንዳለባቸው ነው ለአማራ ሚዲያ ማዕከል የገለፁት። እርዳታ አልደረሰንም በሚል ቅሬታ ያቀረበች አንዲት ሴትና አባቷ ተደብድበዋል፤ በተጨማሪም “ሂድና አማራ ክልልን ጠይቅ” በማለት አቶ ሲሳይ ተፈናቃዮችን ሲያንገላቱ እንደነበር ተገልጧል። በተለይ የአማራ እና የደቡብ ብሄረሰብ ተወላጅ የሆኑ ተፈናቃዮች እርዳታው በአግባቡ እየደረሳቸው አለመሆኑ ተጠቅሷል። የእርዳታ ስርጭት ክፍሉንና የከንቲባውን አድራሻ እንዳገኘን ተጨማሪ ምላሻቸውን አካተን የምንመለስ መሆኑን ስንገልፅ በቅሬታው ላይ ምላሽ ለመስጠት የሚፈልግ ማንኛውንም አካል ተቀብለን የምናስተናግድ መሆኑን በማሳወቅ ጭምር ነው። ፎቶ ፋይል

Source: Link to the Post

Leave a Reply