በኦሮሚያ ክልል አማራዎች ላይ እየተካሄደ ያለው ጥቃት በአስቸኳይ ይቁም! – (ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት)

Source: http://welkait.com/?p=12358
Print Friendly, PDF & Email

(ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት – የቀድሞው ሰማያዊ ሊቀመንበር)

በኦሮምያ ክልል በጎሮ ቀበሌ ጥቃት የተፈፀመባቸው አማራዎች አሁንም ሜዳ ላይ እንደታገቱ ናቸው!!!

ከሁለት ቀናት በፊት በኦሮምያ ክልል በቡኖ በደሌ ዞን ደዴሳ ወረዳ በጎሮ ቀበሌ ይኖሩ የነበሩ አማራዎች በማንነታቸው ምክንያት ቤታቸው፣ ንብረታቸውና ከብቶቻቸው እንደተቃጠለባቸው እና ሜዳ ላይ በክልሉ ልዩ ሃይል ታግተው እንደሚገኙ ገልጨ ነበር። ጥቃት የተፈፀመባቸው 211 አማራዎች ዛሬም የካቲት 10 ቀን 2010 ዓ.ም (February 17 2018) በክልሉ ልዩ ሃይል ታግተው ከአንድ የመስኖ ፕሮጀክት አካባቢ ዛፍ ስር ይገኛሉ። ከእነዚህም ውስጥ በአብዛኛው ህፃናትና ሴቶች ናቸው።

የደንቢ ከተማ ወጣቶችና የአካባቢው ነዋሪዎች ነፍሳቸውን ለማቆየት የበቆሎ ንፍሮ እያቀረቡላቸው እንደሆነ ታውቁዋል። ይህንን በማንነታቸው የደረሰባቸውን ጥቃት በጊዜ እንዲታረም መረጃውን ይፋ በማድረጋችን ይህ ሃቅ ተደብቆ እንዲቀር የሚችሉትን ሁሉ ሲያደርጉ አይቻለሁ። እነዚህ ሰዎች ጥቃቱን ከፈፀሙት ግለሰቦች በላይ ለፖለቲካ ጥቅም ሲሉ በህዝብ ላይ ምንም ነገር ቢፈፀም ደንታ የሌላቸው እና ለመፈፀም ወደ ሁዋላ የማይሉ አረመኔዎች መሆናቸውን አረጋግጫለሁ።

Share this post

One thought on “በኦሮሚያ ክልል አማራዎች ላይ እየተካሄደ ያለው ጥቃት በአስቸኳይ ይቁም! – (ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት)

  1. Yilikal, understand that Oromos have no homogeneous thoughts
    There are some extremists that go against the OPDO principles. It is better you approach ANDM or Lemma Megersa and deliver your concerns. Recently you are becoming a problem in the fight against witness
    You are not politically smart at all. We are talking here about the big picture and are focused on primary foes.

    Reply

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.