በኦሮሚያ ክልል የ2012 ዓ.ም የበጎ ፈቃድ ስራ የእውቅና አሰጣጥ እና የ2013 ዓ.ም የበጎ ፍቃድ ስራ የማስጀመሪያ መርሀግብር እየተካሄደ ነው

በኦሮሚያ ክልል የ2012 ዓ.ም የበጎ ፈቃድ ስራ የእውቅና አሰጣጥ እና የ2013 ዓ.ም የበጎ ፍቃድ ስራ የማስጀመሪያ መርሀግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል የ2012 ዓ.ም የበጎ ፈቃድ ስራ የእውቅና አሰጣጥ እና የ2013 ዓ.ም የበጎ ፍቃድ ስራ የማስጀመሪያ መርሀግብር እየተካሄደ ይገኛል።

የእውቅና አሰጣጥ መርሀግብሩ በክልሉ ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ቢሮ የተዘጋጀ ሲሆን፥ በክልሉ በ2012 ዓ፡ም የክረምት በጎ ፍቃድ ስራ ላይ በግንባር ቀደምትነት ለሰሩ ወጣቶች እና ሴቶች እንዲሁም ስራውን በተሻለ ላስተባበሩ ዞኖች እና ከተሞች እውቅና መስጠትን ታሳቢ ያደረገ ነው።

በመርሀ ግብሩ ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒን ጨምሮ በየደረጃው ያሉ ሌሎች የክልሉና የፌደራል የስራ አመራሮች እንዲሁም የወጣት እና የሴት አደረጃጀቶች ተገኝተዋል።

በክልሉ በ2012 ዓ.ም ክረምት 9 ነጥብ 5 ሚሊየን ወጣቶች እና ሴቶች በአምስት አይነት የበጎ ፍቃድ መርሀግብሮች ተሳትፈው 2 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ግምት ያለው ስራ መስራታቸውን የክልሉ ሴቶች ህፃናት እና ወጣቶች ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ሰአዳ ኡስማን ተናግረዋል፡፡

በዚህም 31 ነጥብ 3 ሚሊየን የህብረተሰብ ክፍሎች በበጎ ፈቃድ ስራው ተጠቃሚ መሆናቸውንም ነው የተናገሩት።

በትዝታ ደሳለኝ

The post በኦሮሚያ ክልል የ2012 ዓ.ም የበጎ ፈቃድ ስራ የእውቅና አሰጣጥ እና የ2013 ዓ.ም የበጎ ፍቃድ ስራ የማስጀመሪያ መርሀግብር እየተካሄደ ነው appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply