በከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል የተጠረጠሩት የደህንነት ከፍተኛ ሹሞች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/73452

በከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል የተጠረጠሩት አቶ መዓሾ ኪዳኔና አቶ ሀዱሽ ካሳ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ (ኢፕድ)

የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮች የነበሩት አቶ መዓሾ ኪዳኔ እና አቶ ሀዱሽ ካሳ ዛሬ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10 የወንጀል ችሎት ቀርበዋል።
በፍርድ ቤቱ በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ከፍተኛ አመራር ናቸው የተባሉት አቶ መዓሾ ኪዳኔና አቶ ሃዱሽ ካሳ ጠበቃ ለማቆም አቅም የለንም ማለታቸውን ተከትሎ መንግስት ጠበቃ እንዲያቆምላቸው በመሃላ አረጋግጠዋል።
መርማሪ ፖሊስ 1ኛ ተጠርጣረ መዓሾ ኪዳኔን ከኦነግ፣ ኦብነግ እና ግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የተጠረጠሩትን ግለሰቦች ከጌታቸው አሰፋ ጋር ተመሳጥረው ያለአግባብ በማሰርና በመደብደብ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት በመፈፀም የሰብዓዊ መብት ጥሰት በማድረስ እና ያለአግበብ ሶሰት መኖሪያ ቤቶችን በማፍራት እንደጠረጠራቸው ገልጿል።
ተጠርጣሪው አቶ መዓሾ በበኩላቸው ትግሬ በመሆኔና በፖለቲካ ውሳኔ ነው የታሰርኩት፤ ከዚህ በፊት በታታሪነት የተሸለምኩ ነኝ፤ አሁን በቱርክ ኢስታንቡል በዲፕሎማትነት ተሹሜያለሁኝ፤ ያሰርኩትም ሆነ የበደልኩት የለም ብለዋል ለችሎቱ።
2ኛ ተጠርጠሪ አቶ ሃዱሽ ካሳ ላይ በተመሳሳይ ፖሊስ ያለአግባብ ዜጎችን በማሰር፣ በመደብደብ እና ተገቢ ያልሆነ ሃብት በቤተሰቦቻቸው ውክልና በመስጠት አካብተዋል ብሎ መጠርጠሩን ነው ለችሎቱ ያብራራው።
1ኛ ተጠርጣሪ አቶ መዓሾ እኔ በዳሪክተር ደረጃ ስራዎችን በማስተባበር የኦፕሬሽን ዘርፍ ሰራተች ሃላፊ እንጂ አሳሪ አደለሁም ብለዋል።
2ኛ ተጠርጣሪ አቶ ሃዱሽ ካሳ በበኩላቸው እኔ ሃላፊነቴ የጽዳት የተሽከራካሪ እና የአትክልት ስራ ቁጥጥር እንጂ የማሰርም ሆነ የማሰቃየት ሃላፊነት የለኝም ይህ እኔን ለማጥቃት ነው

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.