በወላይታ ዞን የተከሰተው ግጭት

https://gdb.voanews.com/1E4F7951-97A9-4E0F-AEE3-36436EDAD705_cx0_cy10_cw0_w800_h450.jpg

በወላይታ ዞን በተከሰተ ግጭት የአምስት ሰዎች ህይወት ማልፉንና ቁጥራቸውን ያልገለጡት ሌሎች ሰዎችም መጎዳታቸውን የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ርስቱ ይርዳው አስታውቀዋል።

“መንግሥት የህዝቡን ጥያቄ ለመመለስ በልዩ ትኩረት እየሠራ ባለበት በዚህ ወቅት ተፈጠረ” ያሉት ሁኔታ እንዳሳዘናቸው ለክልሉ መንግሥት ቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

የዞኑ ነዋሪዎች ትናንት ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ከፀጥታ አስከባሪዎች ጋር በተፈጠረ ግጭት የተገደለው ሰው አሥር እንደሆነ ተናግረው ነበር።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply