በወራቤ ዩኒቨርስቲ በተከሰተ ግጭት ከ5 በላይ ተማሪዎች መጎዳታቸው ተገለጸ።

Source: https://mereja.com/amharic/v2/124340

በወራቤ ዩኒቨርስቲ በተከሰተ ግጭት ከ5 በላይ ተማሪዎች መጎዳታቸው ተገለጸ። ( ኢትዮ 360 )
በዚሁ ግጭት የተነሳ አብዛኞቹ ተማሪዎች ዩኒቨርስቲውን ለቀው መውጣታቸውን ለኢትዮ 360 ከስፍራው የደረሰው መረጃ ያመለክታል።ባለፈው እሁድ ተቀሰቀሰ የተባለው ይሄ ግጭት መነሻ የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ አራት ተማሪዎች ላይ የዩኒቨርስቲው አስተዳደር የወሰደው የዲሲፒሊን ርምጃ መሆኑም ተገልጿል።
Image result for werabe university
ይሄ ርምጃ ያስቆጣቸው የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች በተቋሙ ወስጥ በብሔር ላይ ያንጣጠረ ጥቃት ለመፈጸም ዝግጅት እየተደረገ ነው በሚል ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።ይሄ በሁለት ወገን የተከፈለ ውዝግብ ወደ ግጭት ተቀይሮ አምስት የሚሆኑ ተማሪዎች ተጎድተው ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል።ይሄንኑ ግጭት በመሸሽ በርካታ ተማሪዎች በአካባቢው ወዳለው ጫካ ሲሸሹ ሊሎች ደግሞ ግቢውን ለቀው መውጣታቸውን ከደረሰን መረጃ ለማወቅ ተችሏል።

መረጃዎች እንደሚያመላክቱት ከተነሳው ግጭት ጋር ተያይዞ የመማር ማስተማሩ ሒደት ተስተጓጉሏል።
የተቋሙ አስተዳደር በስተመጨረሻ ወደ ዩኒቨርስቲው ልዩ ሃይል እንዲመጣ ቢያደርግም ልዩ ሃይሉ ግን ችግር ፈጣሪዎቹን ሳይሆን በመሸሽ ላይ ያሉ ተማሪዎችን ሰብስቦ ማሰሩን ነው የመረጃ ምንጮቻችን የገለጹልን።
እስካሁን ምን ያህል ተማሪዎች በልዩ ሃይሉ ተይዘው ስለመታሰራቸው በውል አልታወቀም።
የውራቤ ዩኒቨርስቲ አስተዳደር አግኝቶ ለማነጋገር ኢትዮ 360 ያደረገው ጥረት አልተሳካም።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.