በወያኔና ኦነግ ሕገ መንግሥትም ቢሆን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ዓርማ የሌለው አረንጓዴ፣ ቢጫና፣ ቀይ ሶስት ቀለማት ያሉት ሰንደቅ ዓላማ ብቻ ነው!

Source: https://mereja.com/amharic/v2/203015

በወያኔና ኦነግ ሕገ መንግሥትም ቢሆን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ዓርማ የሌለው አረንጓዴ፣ ቢጫና፣ ቀይ ሶስት ቀለማት ያሉት ሰንደቅ ዓላማ ብቻ ነው! – Achamyeleh Tamiru
Image may contain: textየኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ በማውለብለባችሁ በኦነጋውያን እየተሰቃያችሁ ያላችሁ ወገኖቻችን ሆይ! ይህን ጽሑፍ በጥሞና አንብቡና ሕገ መንግሥት ተብዮውን ካላከበረራችሁት ሞተን እንገኛለን የሚሉትን ኦነጋውያንን ሕገ መንግሥት ተብዮውን እንዲያከብሩ ጠይቋቸው።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰንደቅ ዓላማ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ሶስት ቀለማት ናቸው። የሰንደቅ ዓላማው ሦስቱ ቀለማት እኩል ሆነው አግድም የተቀመጡ ሲሆን ምሳሌያቸውም አረንጓዴው ተስፋ፣ ልምላሜና ሀብት፤ ቢጫው ሃይማኖት፣ አበባና ፍሬ፤ ቀዩ ደግሞ ፍቅር፣ መስዕዋትናነትና ጀግንነት ነው። አንዳንድ ሲባል የሰሙትን ሳይመረምሩ የሚደግሙ ካድሬዎች ይህንን የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰንደቅ ዓላማ «ልሙጡ ሰንደቅ ዓላማ» ወይም «የድሮው ሰንደቅ ዓላማ» እያሉ ይጠሩታል። ይህ ግን የደጋሚዎቹን አጥልቆ ያለማሰብ ችሎታና አለማንበባቸውን እንጂ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰንደቅ ዓላማን ትናንትና ዛሬ የሚያሳይ አይደለም።
ሕገ መንግሥት ተብዮው አንቀጽ ሶስት ስለ ኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ የሚከተለውን ደንግጓል፤
______________________
አንቀጽ ፫
የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ
1. የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ከላይ አረንጓዴ፣ ከመሐል ቢጫ፣ ከታች ቀይ ሆኖ በመሐሉ ብሔራዊ ዓርማ ይኖረዋል። ሦስቱም ቀለማት አኩል ሆነው በአግድም ይቀመጣሉ።
2. ከሰንደቅ ዓላማው ላይ የሚቀመጠው ብሔራዊ ዓርማ የኢ ትዮጵያ ብሔሮች ፣ ብሔረሰቦች ፣ ሕዝቦች አና ሃይማኖቶች በእኩልነትና በአንድነት ለመኖር ያላቸውን ተስፋ የሚያንጸባርቅ ይሆናል።
3. የፌዴራሉ አባሎች የየራሳቸው ሰንደቅ ዓላማና ዓርማ ሊኖራቸው ይችላል። ዝርዝሩን በየራሳቸው ምክር ቤት ይወስናሉ።
______________________
አማርኛ ለሚችል ማንኛውም ሰው የሕገ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.