በዓለ ጥምቀቱ እና የደበኞቹ ነገር !

Source: https://mereja.com/amharic/v2/204545

በዓለ ጥምቀቱ እና የደበኞቹ ነገር !
በዓለ ጥምቀቱ በዛሬው ዕለት የቅዱስ ሚካኤል ታቦትን አጅቦ በማስገባት ይጠናቀቃል። እንኳን አደረሳችሁ ተባብለን መልካም ምኞት ተለዋውጠናል። በበዓሉ አከባበር ወቅት ጎንደር ላይ ምዕመኑ የተቀመጠበት ርብራብ ተደርምሶ የወገኖቻችን ውድ ሕይወት ጠፍቷል፣ አካላዊ ጉዳት ደርሷል። እግዚአብሔር የሞቱትን ነፍስ ይማር፣ ቤተሰብን ያበርታ፤ የተጎዱትንም ይዳብስልን።
ከተፈጥሮ አደጋው መለስ ስንል ግን ዛሬም ሰው ሠራሽ አደጋዎች ቀጥለዋል። የመዲናችንን አንዳንድ አከባቢዎች ጨምሮ በሐረርና ድሬዳዋ… ደግሞ ከሕግና ስርዓት በላይ የሆኑ አካላት የፈለጋቸውን አድርገዋል። ዜጎች የዕምነት ሥርዓታቸውን እንዴት ማክበር እንዳለባቸው፣ የቤተ ዕምነታቸው ንዋየ ትውፊታትና ሌሎች የበዓሉ ማድመቂያ ዕሴቶች በፖሊስ ሃይል፣ ስፖንሰር በሚደረጉ የየአካባቢው ጎረምሶችና ለኢትዮጵያ ጥፋት 24 ሰዓት እየሠሩ ባሉ አካላት እየተወሰነ እንዳለ በአደባባይ ታይቷል።
በመንግሥት በኩል ችግሮችን ለማስወገድ የአቅም ሳይሆን ዝቅ ሲል ቁርጠኝነት፤ ከፍ ሲል ፈቃደኝነት ያለመኖሩ በይፋ ተጋልጧል። (ከወር በፊት ከፍተኛ መጠን ያለው የኦሮሚያ ልዩ ሃይል ሲመረቅ ችግሮች ሁሉ የሚወገዱ፤ ቢያንስ በእጅጉ የሚቀንሱ መስሎኝ ያልተሟገትኩት አልነበረም። አፉ በሉኝ !)
በቤተ ክርስቲያናችን ቃለ አዋዲ(ስርዓተ ቤተክርስቲያንንና ሌሎች) መሰረት ቤተክርስትያኗ የራሷ አርማ ያላት ሲሆን አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ሰንደቅ መሰረቱ በመጽሐፍ ቅዱስ (በዘፍጥረት መጽሐፍ 9:1-17) እግዚአብሔር ለሰው ልጆች በቀስተደመና ተምሳሌት ዘለዓለማዊ የምህረት ቃል ኪዳን የገባበት መሆኑን የገለጸበት ነው።
ሃይማኖታዊና የሕግ ዝርዝር ሳያስፈልገው ግን ዜጎች በአገራቸው፤ የሌሎችን ዕምነትና ማሕበራዊ ዕሴቶች እስካልነኩ ድረስ ዕምነታቸውን በፈለጋቸው መንገድ የማክበር የማይገሰስ መብት አላቸው። እንዴት ዕምነታችንን ማራመድ እንዳለብን፤ አንድ ቀን እንኳ የፈጣሪን

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.