በዕፅ ዝውውር የተጠረጠረችው ናዝራዊት ለመጀመሪያ ጊዜ ቻይና ፍርድ ቤት ቀረበች

Source: https://mereja.com/amharic/v2/132840

BBC Amharic : እፅ በማዘዋወር ተጠርጥራ ቻይና ጉዋንዡ እስር ቤት የምትገኘው ኢትዮጵያዊቷ ናዝራዊት አበራ ከወር በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት መቅረቧንና የመጨረሻውን ፍርድ እየተጠባበቁ እንደሆነ እህቷ ቤተልሔም አበራ ለቢቢሲ ገለፁ።
ናዝራዊት አበራ በቻይና በእፅ ዝውውር ተጠርጥራ በቁጥጥር ሥር መዋሏ ከተሰማ ስድስት ወራቶች አልፈዋል።
አንድ ሰው እፅ ሲያዘዋውር ከተገኘ የሞት ፍርድ እንዲበየንበት የሚያዘው የቻይና ህግ በናዝራዊት ላይ ተግባራዊ ይሆናል በሚል በቤተሰቦቿ፣ በቅርብ ዘመዶቿ እንዲሁም በበርካታ ሰዎች ዘንድ ጋትን አሳድሯል።
ጉዳዩንም ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት እንዲሁም ታዋቂ ግለሰቦች በቅርበት እየተከታተሉት እንደሆነም መገለፁ ይታወሳል።
በቻይና ጉዋንዡ እስር ቤት የምትገኘው ናዝራዊት ባለፈው ወር ሰኔ 20 ቀን 2011 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርባለች። 5.2 ኪሎግራም የሚመዝነውን በሻምፖ መልክ የተያዘጋጀ ኮኬይን የተሰኘ እፅ ማን እንደሰጣትና እንዴት ልትያዝ እንደቻለች ለአገሪቱ ፍርድ ቤት አስረድታለች።
የቻይና መንግሥት ያቆመላት ጠበቃም ናዝራዊት ከአገር ወጥታ እንደማታውቅ የሚያሳይ የጉዞ ታሪክ ማስረጃ፣ ከወንጀል ነፃ መሆኗን፣ የትምህርቷንና የሥራዋን ሁኔታ -ኢንጂነር እንደሆነች የሚያመለክት ማስረጃ መቅረቡን እህቷ ቤተልሔም አበራ ገልፀውልናል።
እህቷ ማስረጃዎቹን የቀረበባትን ክስ ለመከላከል የላኩት መሆኑን በመጥቀስ “የቻይና ሕግ ከባድ ሳይሆን አይቀርም፤ እንዳሰብነው እየሄደ አይደለም ግን ተስፋ አንቆርጥም” ብለዋል።
በሌላ በኩል አቃቤ ሕግ ሆነ ብላ ድርጊቱን እንደፈፀመችና የተማረች ሆና ሳለ በስህተት ይህን መቀበል አልነበረባትም ሲል ክሱን ማሰማቱን ነግረውናል።
“በድጋሚ መቼ ፍርድ ቤት እንደምትቀርብ ቁርጥ ያለ ቀን አይታወቅም” የሚሉት እህቷ ቤተልሔም በቻይና

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.