“በዘላቂነት ከማንኛውም የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ጥቃት ራሳችን መከላከል የምንችለው በነቃ እና በበቃ ሁኔታ ተደራጅተን መታገል ስንችል ነው” ሲል የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ/አ…

“በዘላቂነት ከማንኛውም የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ጥቃት ራሳችን መከላከል የምንችለው በነቃ እና በበቃ ሁኔታ ተደራጅተን መታገል ስንችል ነው” ሲል የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ/አ…

“በዘላቂነት ከማንኛውም የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ጥቃት ራሳችን መከላከል የምንችለው በነቃ እና በበቃ ሁኔታ ተደራጅተን መታገል ስንችል ነው” ሲል የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ/አዴሃን አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መስከረም 7 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ/አዴሃን ዛሬ ባወጣው መግለጫ “መንግስት የዜጎችን ሠላም እና ደህንነት የማስጠበቅ ኃላፊነቱን ይወጣ” ሲል በተደጋጋሚ ማሳሰቡን አስታውቋል። መንግስት ያለ ምንም ሰበብ የህግ የበላይነትን ማስከበር እንዳለበት በተደጋጋሚ ስናሳስብ ቆይተናል ያለው የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ/አዴሃን ይሁን እንጅ መንግስት የህግ የበላይነትን ማስከበር ባለመቻሉ የሀገር አንድነትን አደጋ ውስጥ የሚጥሉ በርካታ ክስተቶች በተደጋጋሚ ሲፈፀሙ ቆይተዋል ብሏል። የህግ የበላይነት ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ቀሪ የመንግስት ተግባራትን ማከናወን እንደማይቻል የገለፀው አዴሃን ሌሎች የፖለቲካ ምክንያቶች እንዳሉ ሆነው የህግ የበላይነት ባለመከበሩ በሀገራችን ኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ዜጎች በማንነታቸውና በሃይማኖታቸው ተለይተው ዘግናኝ ጥቃት ሲደርስባቸው ቆይቷል ሲልም አክሏል። ከሰሞኑ ደግሞ በመተከል በተመሳሳይ ንፁሃን ዜጎች በአስቃቂ ሁኔታ ህይወታቸውን አጥተዋል ያለው ድርጅቱ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ በተለየ ሁኔታ በአማራዎች ላይ በደረሰው ጭፍጨፋ በመንግስት መዋቅር ውስጥ ያሉ አመራሮችን ጨምሮ በፀረ አማራ እና በፀረ ኢትዮጵያ ትርክት የፖለቲካ መስመራቸውን ያሰመሩ ፅንፈኞች የተቀናጀ ድርጊት መሆኑን ለማወቅ መቻሉን አስታውቋል። አዴሃን መንግስት ውስጡን በመፈተሽ ጭምር ሃላፊነቱን በተግባር መወጣት እንዳለበት ነው በጥብቅ ያሳሰበው። መንግስት መንግስታዊ ተግባሩን ባለመወጣቱ የዜጎችን ሠላም እና ደህንነት ባለማስጠበቁ ለደረሰው ጉዳት ሁሉ የመጀመሪያው ተጠያቂ መንግስት መሆኑን አጥብቀን ማሳቅ እንፈልጋለን ሲል የገለፀው ድርጅቱ ሕዝባችን በዘላቂነት ከማንኛውም የፖለቲካ የኢኮኖሚ የማህበራዊ ጥቃት ራሳችን መከላከል የምንችለው በነቃ እና በበቃ ሁኔታ ተደራጅተን መታገል ስንችል መሆኑን ማስገንዘብ እንወዳለን ብሏል። ስለሆነም ላለፉት አመታት በትጥቅ ትግል በኤርትራ በረሃ አሁን ደግሞ በሠላማዊ ትግል ታግሎ የሚያታግልህን ድርጅት የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ/አዴሃንን በመቀላቀል በሀሳብ በማቴሪያል በማገዝ የበኩላችሁን አስተዋጽኦ ታደርጉ ዘንድ በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን ሲል ነው ጥሪ ያቀረበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply