በዚህ ዓመት ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀው ጠቅላላ ምርጫ ከሌሎች አገሮች ጣልቃ ገብነት የፀዳ እንዲሆን ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት የቻይና አምባሳደር አሳሰቡ፡፡

Source: https://mereja.com/amharic/v2/191677

Reporter Amharic

በዚህ ዓመት ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀው ቀጣዩ ጠቅላላ ምርጫ ከሌሎች አገሮች ጣልቃ ገብነት የፀዳ እንዲሆን ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት፣ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ታን ጂያን አሳሰቡ፡፡
አምባሳደሩ በኢትዮጵያ በኩል የተለየ ለውጭ ጣልቃ ገብነት የሚዳርግ ሥጋት ባይኖርም፣ ያደጉ አገሮች በአንድ አገር የውስጥ ፖለቲካ መግቢያ ምክንያታቸው ብዙ ስለሆነ ነቅቶ መጠበቁ የተሻለ ነው ብለዋል፡፡
ጣልቃ ገብነቱ በአብዛኞቹ ታዳጊ አገሮች ላይ የሚሞከርና የተለመደ መሆኑን የገለጹት አምባሳደር ታን፣ ያደጉት አገሮች የሰብዓዊ መብት ጥበቃን ሰበብ አድርገው የራሳቸውን አጀንዳ እንዲያራምዱ ታዳጊ አገሮች መፍቀድ የለባቸውም ብለዋል፡፡
የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ጉዳዮችን ሰበብ አድርገው በታዳጊ አገሮች የውስጥ ጉዳይ እጃቸውን የሚያስገቡ አገሮች የሚመፃደቁትን ያህል የሰብዓዊነት መብት ጥበቃ ታሪክ የላቸውም ብለዋል፡፡ በታሪክ የማይዘነጉ አሰቃቂ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ያደርሱ የነበሩ ናቸው ሲሉም አክለዋል፡፡
እንደ ኢትዮጵያና ቻይና ያሉ ታዳጊ አገሮች የራሳቸው የሰብዓዊ መብት አረዳድ ያላቸው፣ ጽንሰ ሐሳቡን ለመረዳት የሌሎችን መሪነት የማይሹ ሉዓላዊ አገሮች እንደሆኑ የተናገሩት፣ የሁለቱን አገሮች ትብብርና ቻይና በመጪው ዓመት በኢትዮጵያ ልትሠራ ያቀደቻቸውን ፕሮግራሞች በተመለከተ፣ ዓርብ ታኅሳስ 17 ቀን 2012 በቻይና ኤምባሲ ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው፡፡
የሁለቱ አገሮች ትብብር በተለይም በኢኮኖሚው ዘርፍ ጠንክሮ እንደሚቀጥል፣ በኢትዮጵያ ኢንቨስት በማድረግም ረገድ የቻይና ኢንቨስተሮች ቀዳሚ መሆናቸውን፣ ባለፉት አሥር ወራት ብቻ 147 የቻይና የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ኢትዮጵያ መቀበሏን ገልጸዋል፡፡
በውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት የቻይና ኢንቨስተሮች ተሳትፎም በየዓመቱ በ12.2 በመቶ እያደገ መምጣቱ ተናግረዋል፡፡ በዚህ ዓመት ኢትዮጵያ ከተቀበለቻቸው የውጭ ቀጥታ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.