በየመን በአንድ ገበያ ላይ በተፈጸመ ጥቃት 12 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ተገደሉ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/189152

The United Nations has condemned an airstrike on a busy market that killed at least 17 people earlier this week in northern Yemen, a region which has been under control of Yemen’s Iran-backed rebels known as Houthis.
በሰሜናዊ የመን ሳዳ ግዛት በአንድ ገበያ ላይ በተፈጸመ ጥቃት አስራ ሁለት ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ጨምሮ አስራ ሰባት ሰዎች መገደላቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ። ጥቃቱ የሑቲዎች ጠንካራ ይዞታ በሆነው የሳዳ ግዛት በሚገኝ አል-ራቅው የተባለ ገበያ ላይ የተፈጸመው ባለፈው ማክሰኞ ነበር። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሌሎች አስራ ሁለት ሰዎች ለቆሰሉበት ጥቃት ተጠያቂ ያደረገው ወገን የለም።
የድርጅቱ የሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪ ሊዜ ግራንዴ አስራ ሁለት ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ጨምሮ አስራ ሰባት ሰዎች መገደላቸውን እና ሌሎች አስራ ሁለት መቁሰላቸውን ገልጸዋል።
ሊዜ ግራንዴ «በአል-ራቅው ገበያ የተፈጸመው ጥቃት በግጭቱ እጃቸውን ያስገቡ ኃይሎች ለዓለም አቀፍ ሕግጋት መከበር ባላቸው ቁርጠኝነት ላይ አሳዛኝ ጥያቄዎች ይጭራሉ» ብለዋል።
ሳዑዲ አረቢያ መራሹ ግብረ-ኃይል ገበያው በሚገኝበት ሞናቢህ የተባለ አካባቢ ድብደባ መፈጸሙን አረጋግጧል። የጥምር ኃይሉ ቃል አቀባይ ቱርኪ አል-ማሊኪ የደረሰ ጉዳት ካለ ምርመራ ይደረጋል ቢሉም ተጨማሪ መረጃ ከማቅረብ ተቆጥበዋል።
ባለፈው ሳምንት በዚያው አካባቢ በተፈጸሙ ሁለት የተናጠል ድብደባዎች ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ጨምሮ 20 ሰላማዊ ሰዎች ተገድለው እንደነበር የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።
ባለፈው ወር በዚያው በየመን በተፈጸሙ ጥቃቶች 60 ሰዎች ሳይሞቱ ወይም ሳይቆስሉ እንዳልቀረ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታውቋል። ( ጀርመን ራዲዮ/DW )

UN condemns attack that killed 17 civilians in north Yemen


https://www.japantimes.co.jp/news/2019/12/26/world/u-n-condemns-attack-killed-17-civilians-north-yemen/

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.