በደቡባዊ አፍሪካ በተከሰተ አውሎንፋስ እስከአሁን 150 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል

Source: https://fanabc.com/2019/03/%E1%89%A0%E1%8B%B0%E1%89%A1%E1%89%A3%E1%8B%8A-%E1%8A%A0%E1%8D%8D%E1%88%AA%E1%8A%AB-%E1%89%A0%E1%89%B0%E1%8A%A8%E1%88%B0%E1%89%B0-%E1%8A%A0%E1%8B%8D%E1%88%8E%E1%8A%95%E1%8D%8B%E1%88%B5-%E1%8A%A5/

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በደቡባዊ አፍሪካ በተከሰተ አውሎንፋስ እስከአሁን 150 ሰዎች ህይወታቸውን ማጣታቸው ተሰማ።

አውሎንፋሱ የተከሰተው በሞዛምቢክ፣ በዚምባብዌ እና በማላዊ ሲሆን፥ በሀገራቱ ውስጥ ከሞቱት በተጨማሪ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ደግሞ የት እንደደረሱ አልታወቀም ተብሏል።

እንዲሁም ሳይክሎን ኢዳይ በመባል በሚሰኘው አውሎንፈስ ውስጥ በአስርሺዎች የሚገመቱ ሰዎች በአደጋው ውስጥ እንደሚገኙ ተግልጿል።

የተባበሩት መንገስታትና የአካባቢው ሀገራት መንግስታት እንደገለጹት አውሎንፋሱ በነዚህ ሦስት ሀገራት ውስጥ  የሚኖሩ በጥቅሉ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ዜጎች ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር አስታውቀዋል።

በአውሎንፋሱ የኤሌክትሪክ ኋይል፣ ትምህርት ቤት መኖሪያ ቤቶች በርካታ መሰረተ ልማቶች መውደማቸው ተነግሯል።

አውሎንፋሱ ያስከተለው ከባድ ጎርፍም የአየር ማረፊያዎችን ድልድዮችን በማውደሙ የነፍስ አድን ስራውን አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደከተተው ተገልጿል።

የተባበሩት መንግስታትና የቀይመስቀል ማህበር በሦስቱም ሀገራት በሂሊኮፕተር የታገዘ የሰብዓዊ እርዳታ እያደረጉ መሆኑን አስታውቀዋል።

 

ምንጭ፦ሲጂቲኤን

በአብርሃም ፈቀደ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.