በደቡብ አፍሪካ የባቡር አደጋ የተጎዱ ሰዎች ቁጥር ከ 200 በላይ እንደሆነ ተነገረ

Source: http://amharic.abbaymedia.info/archives/41206

አባይ ሚዲያ ዜና
አቤነዘር አህመድ

በደቡብ አፍሪካ ጀርሚስቶን ከተማ ሁለት ባቡሮች ተጋጭተው በደረሰው አደጋ በርካታ ሰዎች መጎዳታቸው ተዘገበ።

ከጁሃንስበርግ 20 ኪሜ በስተምስራቅ በምትገኘው በዚች ከተማ በደረሰው አደጋ ወደ 226 የሚደርሱ ሰዎች መጎዳታቸው ተገልጿል።

በደረሰው አደጋ የሞተ ሰው እንደሌለ  የደቡብ አፍሪካ የአደጋ ጊዜ ቢሮ በሰጠው መግለጫ አሳውቋል። በአደጋው የተጎዱት አብዛኞዎቹ ለህይወት የሚያሰጋ ጉዳት እንዳላጋጠማቸውም ተገልጿል።

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ እንደሆነ ሲገለጽ፤ የአይን እማኞች አደጋ የደረሰበት አንደኛው ባቡር ቆሞ እንደነበረ ጠቅሰዋል።

በደቡብ አፍሪካ ከሳምንት በፊት ባቡርና መኪና ተጋጭተው 19 የሚደርሱ ሰዎች ህይወታቸው ሲያጡ ከ250 በላይ መጎዳታቸው ይታወሳል።

ከ2016 እስከ 2017 እኤአ ባለው ጊዜ በደቡብ አፍሪካ በባቡር አደጋ 495 ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጡ ወደ 2,079 ሰዎች መጎዳታቸውን ሪፖርቶች ያሳያሉ።

 

Share this post

Post Comment