በደቡብ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ የሚመራ ልዑክ አሜሪካ ገባ

Source: https://fanabc.com/2019/12/%E1%89%A0%E1%8B%B0%E1%89%A1%E1%89%A5-%E1%8A%AD%E1%88%8D%E1%88%8D-%E1%88%9D-%E1%88%AD%E1%8B%95%E1%88%B0-%E1%88%98%E1%88%B5%E1%89%B0%E1%8B%B3%E1%8B%B5%E1%88%AD-%E1%8A%A0%E1%89%B6-%E1%88%AD%E1%88%B5/

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 28 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው የሚመራ ልዑክ በዛሬው ዕለት አሜሪካ ገብቷል፡፡

በልዑኩ በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስተሩ አማካሪን ጨምሮ የተለያዩ የስራ ሃላፊዎች ተካተዋል፡፡

ልዑኩ ወደ አሜሪካ ያቀናው ንግድና ኢንቨስትመንትን ለማስተዋወቅ እንዲሁም የክልሉ ተወላጅ የሆኑ ዳያስፖራዎች በክልሉ ብሎም በሀገሪቱ ልማት ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማበረታታ መሆኑን አምባሳደር ፍፁም አረጋ አስተውቀዋል፡፡

ልዑክ ዋሺንግተን ሲደርስ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አምባሳደር ፍፁም አረጋ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.