በደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ የምትገኘው የግሸን ደብረ ከርቤ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም እንዲከበር አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መስከረም 21 ቀን 20…

በደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ የምትገኘው የግሸን ደብረ ከርቤ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም እንዲከበር አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በእያመቱ በድምቀት የምትከበረው በደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ የምትገኘው የግሸን ደብረ ከርቤ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም እንዲከበር አስፈላጊው ዝግጅት ሁሉ መደረጉን የደቡብ ወሎ ዞን ሠላምና ደህንነት ጉዳዮች መምሪያ አስታውቋል። በዓሉ እንደወትሮው ሁሉ ነገ መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ም በታላቅ ድምቀት የሚከበር መሆኑ ተገልጧል። በበዓሉ በርካታ የክርስትና እምነት ተከታዮች በሥፍራው ላይ የተገኙ ሲሆን የጸጥታ ችግር እንዳያጋጥም አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጎ እየተሠራ መሆኑን የደቡብ ወሎ ዞን ሠላምና ደህንነት ጉዳዮች መምሪያ ማስታወቁን የደቡብ ወሎ ብልፅግና ጽ/ቤት በገጹ አስፍሯል። በዘንድሮው የግሸን ደብረ ከርቤ ዓመታዊ የንግሥ በዓል ላይ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ምዕመን እንደሚገኝ ቅድመ ግምቱን ያስቀመጠው የደቡብ ወሎ ዞን ባህል እና ቱሪዝም መምሪያም በዓሉን ያለምንም እንከን ለማክበር የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ማጠናቀቁን ከቀናት በፊት መግለፁ ይታወሳል። የዞኑ የባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ አቶ ሱለይማን እሸቱ ባለፈው ዓመት ሦስት ሚሊዮን የሚጠጋ ምዕመን ወደግሸን መምጣቱን አስታውሰው፤ ዘንድሮ ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭት ጋር ተያይዞ ምዕመኑ በግማሽ ሊቀንስ ይችላል የሚል ግምታቸውን ለአብመድ መግለጻቸው አይዘነጋም።

Source: Link to the Post

Leave a Reply