በደብረታቦር ከተማ የንጉሰ ነገስት የዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ ሃውልት ተሰርቶ ተመረቀ

Source: http://welkait.com/?p=12089
Print Friendly, PDF & Email

በደብረታቦር ከተማ የንጉሰ ነገስት የዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ ሃውልት ተሰርቶ ተመረቀ

በደብረታቦር አደባባይ ላይ በ7 ሜትር ከ50 ከፍታ በክብር ከልጁ ልዑል አለማየሁ ቴዎድሮስ ጋር የቆመው ያዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ ሀውልት ተመረቀ።

“የአፄ ቴዎድሮስን የእውቀት ጥያቄ የመመለስ ታሪካዊ ሃላፊነት አለብን” ይህ ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ግቢ መግቢያ በር ላይ በጉልህ ተጽፎ ይነበባል።

አፄ ቴዎድሮስ ከጦረኛነታቸውና ኢትዮጵያን አንድ ከማደረግ ህልማቸውም ጎን ለጎን ለቴክኖሎጅ የነበራቸው እይታ አንቱታን ካተረፉባቸው መወደሻዎቻቸው መካከል ይጠቀሳሉ።

በደብረታቦሩ አዲስ ሀውልት ይህ ራዕያቸው ታሳቢ ተደርጎ ነው የቆመላቸው።

ሀዉልቱ ከነ መቆሚያዉ 7. 50 ሜትር ርዝመት ሲኖረው 80 ሺህ ሊትር ውሃ የሚይዝ ፋውቴን ገንዳም አለው።

“የሀውልቱ ሀሳብ የአፄ ቴወድሮስ የሞቱለትን የውቀት ጥያቄ ማንፀባረቅ ነው። ይህ ማለት ንጉሰ ለሀገር አንድነት ካበረከቱት ስራ በተጨማሪ የሞቱለት የዉት ጥያቄ መሆኑን ግንዛቤ መፋጠር” ይህንን ያካፈለን ደ/ታቦር የሚኖር እና ይህ ግንባታ እውን እንዲሆን ይሳተፍ የነበረ የአማራ ወጣት ነው።

ዳግማዊ ቴወድሮስ ንጉሰ ነገስት ዘ ኢትዮጵያ ራዕያቸው ታላቋን ኢትዮጰያ እስከ የመን መመስረት ነበር፡፡ ለ ይህንን አላማ ለማሳካት እንዲያስችላቸውና የሀይል ሚዛኑን ለመቆጣጠር እንዲያመቻቸው በጋፋት የቴክኖሎጅ ተቋም እንዲመሰረት ማድረጋቸው ይታወሳል።

ነገር ግን በወቅቱ ከውጭ የአቢሲንያን ታላቅነት የማይፈልጉ ከውስጥ ደግሞ የቴዎድሮስን ህልም ያልተረዱ እና የተረዱም ቢሆኑ ከኢትዮጰያዊነት ይልቅ ለባንዳ ያደሩ ሊቃወሟቸው ችለዋል፡፡

ስማቸው እና ስራቸው ክብሩን እንደጠበቀ በትውልዱ ዘንድ ያሉት ቴዎድሮስ ደብረታቦር ላይ በሀውልታቸው ከፍ ብለው ይታያሉ።

የአፄ ቴወድሮስን አላማ አንግቦ ራእያቸውን ሰንቆ በመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ መንደር ጋፋት አፋፍ የሴባስቶፖል ወላጅ እናት በሆነችው ደብረታቦር ማማ ላይ በኩራት የቆመው ደብረታቦር ዪኒቨሲቲ ወጭውን መሸፈኑም ታውቋል።

አባቶቻችንና በጎ ተግባራቸውን መዘከር የዚህ ትውልድ ሀላፊነት ነው።

ልሣነ ዐማራ- Amhara Press

 

 


ዳግማዊ ዐፄ ቴዎድሮስ- የዘመናዊት ኢትዮጵያ አስተዳደር ቋሚ መሠረት ጣይ ፡- ዝክረ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ከልደት አስከ ሕልፈተ ሕይዎት።

ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ( አባ ታጠቅ )የዘመናዊት ኢትዮጵያ ምሥረታ ፋናወጊ (በሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት የተዘጋጀ)

መግቢያ፦

ዳግማዊ ዐፄ ቴዎድሮስ ለኢትዮጵያ ክብር፣ ነፃነት፣ ሉዓላዊነትና ብሔራዊ ማንነት ሲሉ፣ እጃቸውን ለእንግሊዝ ጦር መሪ ጄኔራል ናፒየር ከሚሰጡ ሞትን በመምረጥ ሽጉጣቸውን ጠጥተው ለኢትዮጵያዊነት ዳብሮ መቀጠል የተሰው ሰማዕት ንጉሠ ነገሥት መሆናቸው ዓለም ያወቀውና ያደነቀው አንጸባራቂ የታሪካችን አንዱ አካል ነው። ቴዎድሮስ ከእርሳቸው የነበሩት ንጉሦች መሠረታቸውን ይፋት፣ ሐረርና አዳል ባደረጉ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ጋር ባደረጉት ተከታታይ ጦርነቶች፣ ተያይዞም ከግራኝ ጋር በተካሄደው እጅግ አውዳሚ አሥራ አምስት ዓመታት ያስቆጠረ ጦርነት፣ በኋላም የግራኝን እግር በመከተል በተከሰተው የጋላ (ኦሮሞ) ወረራ የሕዝቡ አንድነት ላላቶ፣ የኢኮኖሚ አቅሙ መድቀቅ የተነሳ በተፈጠረው ሁለንተናዊ ድክመት የተከሰተውን የዘመነ መሣፍት አገዛዝ ዘመን የተፈጠሩ የዚያን ወቅት ኅብረተሰብ ልጅ ናቸው። ቴዎድሮስ አገሪቱ በየአካባቢው የጦር አበጋዞች ተሸንሽና፣ የዘውዱ የአንድነት ምልክትነቱና የሥልጣን ምንጭነቱ ጥያቄ ውስጥ ወድቆ ከ70 ዓመታት ላላነሰ በዘለቀው «ዘመነፍዳ» የብላ ተባላ ዘመን፣ በቆራጥነት ታግለው፣ የአገሪቱን አንድነት ትናሣዔ ያበሰሩ ጀግና መሪ መሆናቸው ማንም ሊጠራጠረው ያልቻለ ሥብዕና ባለቤት ናቸው። ለዘመናዊ ኢትዮጵያ አስተዳደር ጽኑ መሠረት የጣሉ፣ ከሁሉም በላይ የዘውዱንና የንጉሠ ነገሥቱን መብትና ሥልጣ መልሶ ተገቢ ቦታውን እንዲይዝ ያደረጉ ራዕየ ሠፊ፤ ብልኅ፣ አስተዋይ፣ ቆራጥና ጀግና ንጉሠ ነገሥት መሆናቸው ይታወቃል።

ይህ ደረቅ ሐቅ ይሁን እንጂ፣ ኢትዮጵያውያን ባለመታደል ይሁን፣ ወይም በእርግማን፣ ወይም በሌሎች በቅጡ በማናውቃቸው ምክንያቶች ለትውልድ ተከታታይነትና ቀጣይነት በሚያገለግሉ መልካም ሥራዎች ላይ መጨመር፣ መልካም የሠሩ ሰዎችን ማሰብና ማሞገስ፣ ባህላችን ባለመሆኑ፣ የዚህ ጀግና መሪ ራዕይ ቀጣይነት አጥቶ፣ እርሳቸው በከፍተኛ መስዋዕትነትና ወደር በሌለው ጀግንነት የገነቡት አንድነት ዛሬ ከ156 ዓመት በኋላ ወደኋላ ተጉዘን በቋንቋ ልዩነት ከዘመነ መሣፍንት በከፋ መልኩ ተከፋፍለን ስንናከስ ማየት ከችግርነቱ አልፎ፣ ባህላችን እየሆነ መምጣቱ ከማሳዘን አልፎ ያሳፍራል ። በዚህ ሁኔታ ከቀጠልን ኢትዮጵያ እንደ አገር፣ ኢትዮጵያዊነት እንደ ዜግነት መታወቂያነት የመቀጠላቸው ሁኔታ ምንም ዓይነት ማስተማመኛ ነገር የለም። ይህ ልዩነት ካለበት ካሁኑ ሁኔታ ሠፍቶ፣ ኢትዮጵያውያን ለመግባባት እንደ አፍሪካ ኅብረት፣ ተመድ ስብሰባዎች አስተርጓሚ የሚያስፈልገን ብቻ ሳይሆን፣ ባንድ አዳራሽ ለመሰብሰብ የምንችልበት ሁኔታ ሩቅ እንደሆነ የልዩነት ጉዞአችን ፍጥነት አመላካች ነው።

ይህ አሳዛኝ ክስተት ከመፈጠሩ በፊት እንደ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ያሉትን የአንድነትና የኢትዮጵያዊነት ምሳሌ የሆኑ ሰዎችን ሥራዎች በማሰብ ትውልዱ ወደ ዕውነተኛው ኅሊናው ተመልሶ በቴዎድሮስ መንፈስና ራዕይ አገሩን እንዲመለከት የዳግማዊ ቴዎድሮስን ሕይዎትና ሥራዎች ለትውልድ ማስታወስ ጠቃሚነቱ የትውልድን ተከታታይነትና ተያያዥነት ስለሚፈጥር ጥቅሙ ዙሪያ ገባ ነው።

በመሆኑም ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት በየዓመቱ በተለያዩ ዝግጅቶች ታስበው እንዲውሉ ስምምነት ካደረገባቸው ቀኖች አንዱ የሆነው፣ ዐፄ ቴዎድሮስ ለኢትዮጵያ ክብርና ነፃነት መጠበቅ ሲሉ ሕይዎታቸውን የሰጡበት ሚያዝያ 6 ቀን በዚህ ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ ታስቦ ይውላል። በዝግጅቱ ከሚቀርቡት አንዱና ዋናው የዳግማዊ ቴዎድሮስ ታሪክና ለኢትዮጵያ አንድነት ያበረከቱት አስተዋጽዖ ይሆናል። …..  (Read More PDF)

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.