በድሬዳዋ ቺኩን ጉንያ የተባለ ወረርሽኝ መከሰቱ ተሰማ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/138056

Imageቺኩን ጉንያ የተባለ ወረርሽኝ በድሬዳዋ መከሰቱ ተሰማ
 
ከሰሞኑ ቺኩን ጉንያ የተባለ በደቃቅ ተህዋሲያን አማካኝነት የሚመጣ በሽታ በድሬድዋ ተከስቷል፡፡ ለበሽታዉ የትንኝ ንክሻ ትክክለኛዉ መንስኤ ነዉ፡፡ የከተማዉ አስተዳደር ባወጣዉ መረጃ በሽታዉ ከቆሻሻ ማጠራቀሚዎች፣ ዉሀ ካቆሩ ቦታዎች፣ ዉሀ ሊይዙ ከሚችሉ ጎማ፣ሸክላ፣ ቆርኪና መሰል ነግሮች እንደዚሁም ለትንኝ የሚያጋልጡ አለባበሶች ሊከሰት ይችላል፡፡

ይህ ደግሞ ለከፍተኛ ትኩሳት፣ የመገጣጠሚያ አካላት ህመም የቺኩን ጉንያ ወረርሽኝ መገለጫዎች ናቸዉ፡፡ በዚህ በሽታ የተጠቃ ሰዉ በፍጥነት ወደ ህክምና ማእከላት ካልሄደ ለሞት ሊያጋለጥ ይችላል፡፡ ስለሆነም የበሽዉ ምልክት የሆኑት ትኩሳት፣ የመገጣጠሚያ ህመም፣ ሽፍታ የታየበት ሰዉ በፍጥነት ወደ ህክምና መሄድ ይኖርበታል አሊያም ሪፖርት ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡

ቺኩን ጉንያ በአለም በምድር ወገብ አካባቢ በአፍሪካ፣ በላቲን፣ ሰሜን አሜሪካና የደቡብ ምስቅ እስያ አካባቢዎች በስፋት ተሰራጭቶ የሚገኝ ሲሆን 2.5 ሚሊየን ሰዉ ለዚህ ተጋላጫ ሆኗል፡፡ በኢትዮጵያም በ2016 አመት በሶማሊ ክልል ዶሎ አዶና በ2019 አፋር አደሬ ተከስቶ ነበር፡፡ እንደዚሁም በዚህ አመት ሰኔ ወር ቀብሪ ደሀርና በደቡብ ክልል ዳዉሮ ተከስቶ ነበር፡፡ በዚህ አመት ደግሞ ተረኛዋ ድሬድዋ እንደሆነች የከተማዋ ጤና ቢሮ አስታዉቋል፡፡

ምንጭ፦ Andafta.com

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.