በዶ/ር አረጋዊ በርሔ የሚመራው የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ከብልጽግና ፓርቲ ጋር ልዋሃድ እችላለሁ አለ፡፡

Source: https://mereja.com/amharic/v2/180570

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ከብልጽግና ፓርቲ ጋር ልዋሃድ እችላለሁ አለ፡፡
ፓርቲው የምስረታ ጉባኤውን ባሳለፍነው ቅዳሜና እሁድ አካሂዶ ስሙን ከትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር ወደ ትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ መቀየሩን አስታውቋል፡፡
ጉባኤውን በማስመልከትም ዛሬ በሰጠው መግለጫ በአላማ ከሚመስሉን የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር እስከ ውህደት በሚያደርስ ትብብር አብሮ ለመስራት ዝግጁ ነኝ ብሏል፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም የትግራይ ህዝብ በአዲሱ የብልጽግና ፓርቲ ውስጥ ተወካይ የሌለው በመሆኑ ፓርቲያችሁ ከገዢው ፓርቲ ጋር ሊዋሃድ ይችላል ተብሎ ይገመታል ምላሻችሁ ምንድነው ሲል ጠይቋል፡፡
እስካሁን ከብልጽግና ፓርቲ ጋር ውህደትን በተመለከተ ያደረግነው ውይይት የለም፤ ነገር ግን የፓርቲውን ፕሮግራም አይተን ልንዋሃድ እንችላለን፡፡ ብልጽግናም በሩ ክፍት መሆኑን እንውቃለን ሲሉ የፓርቲው ከፍተኛ ሊቀመንበር ዶክተር አረጋዊ በርሔ ተናግረዋል፡፡
ዜናው የኢትዮ ኤፍ ኤም ነው

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.