በጃርቴ ወረዳ የአባ ገዳዎችን ቃል በመጣስ 8 የጦር መሳሪያ ነጥቆ ወደ ዘጠነኛው ሲሸጋገር በጥይት ለተገደለ አንድ የኦነግ ሸኔ አባል በመወገን አማራን መግደል፣መዝረፍና ማፈናቀሉ እንደቀጠለ ነ…

በጃርቴ ወረዳ የአባ ገዳዎችን ቃል በመጣስ 8 የጦር መሳሪያ ነጥቆ ወደ ዘጠነኛው ሲሸጋገር በጥይት ለተገደለ አንድ የኦነግ ሸኔ አባል በመወገን አማራን መግደል፣መዝረፍና ማፈናቀሉ እንደቀጠለ ነ…

በጃርቴ ወረዳ የአባ ገዳዎችን ቃል በመጣስ 8 የጦር መሳሪያ ነጥቆ ወደ ዘጠነኛው ሲሸጋገር በጥይት ለተገደለ አንድ የኦነግ ሸኔ አባል በመወገን አማራን መግደል፣መዝረፍና ማፈናቀሉ እንደቀጠለ ነው ተባለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 7 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉድሮ ዞን በተለይም በጃርቴ፣በአሙሩና በደዱ ወረዳዎች የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች የንፁሀንን ደም እያፈሰሱ ነው፤ህጻናትን እያገቱና እየዘረፉ ነው ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። በሀሰት ትርክትና በአማራ ጥላቻ ያደገው የኦነግ ሸኔ ጦር ትናንት የፈፀመው እልቂት አልበቃው ብሎ ዛሬም የአማራ ተወላጆችን እያደነ መግደል፣መዝረፍ፣መድፈርና ማፈናቀሉን ያለማንም ተከላካይ እያስቀጠለ መሆኑን የገለፁት ነዋሪዎች ናቸው። ኦነግ ሸኔ በአካባቢው ንፁሀንን በተለያየ ጊዜ ከጨፈጨፈ በኋላ በጃርቴ ወረዳ ሙሱ በተባለ ቀበሌ ላይ በአባ ገዳዎች አማካኝነት ለመታረቅ ፍቃደኛ ነኝ በማለት የኦነግ ሸኔ መሪ ነው የተባለ ግለሰብን ከነጦሩ በመላክ ጥቅምት 4 ቀን 2013 ዓ.ም ከተሰበሰቡበት ቃሉን በማፍረስ 8 የጦር መሳሪያን በአባ ገዳዎች ፊት ነጥቆ ስለመውሰዱ ነዋሪዎች አውስተዋል። የኦነግ ታጣቂዎች በመቀጠልም በውይይቱ ያልተገኙትን ገበሬዎች ጦር መሳሪያ ለመንጠቅ በሚል ወደ አማራ ሚሊሻዎች ማቅናታቸው ተሰምቷል። በዚህ መሀል “ካልሞትኩ በስተቀር መሳሪያንማ አልሰጥህም” በማለት ከአንድ በአካባቢው ነዋሪ ከሆነ ሚሊሻ በተተኮሰ ጥይት የኦነግ መሪ የተባለው ሰው ተገድሏል። 8 በእርቅ ስም አታሎ እና ቃሉን አፍርሶ የነጠቀው ኦነግ ሸኔ 9ነኛውን መሳሪያ ለመደረብ ባደረገው የተኩስ ልውውጥ ነው የተገደለው ያሉት ምንጮች ይህን ተከትሎ በጃርቴ ወረዳ የኦነግ ደጋፊ ከሆኑ ቄሮዎች ጋር በመሆን በንፁሀን ላይ ግድያ፣ዝርፊያና ማፈናቀሉን እንደገፉበት መሆኑን አክለው ተናግረዋል። እንደአብነትም በትናንትናው እለት ጥቅምት 6 ቀን 2013 ዓ.ም በጠራራ ፀሀይ በጃርቴ ወረዳ ሙሱ ቀበሌ ላይ አንድ የ10ኛ ክፍል የአማራ ተማሪን ስለማረዳቸው ተነግሯል። የኦሮሚያ ክልል ልዩ ሀይልም ሆነ ሌሎች የፀጥታ አካላት ከነፍሰ ገዳዮች እየታደጉን አይደለም ያሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ አማራዎች ተፈናቅለዋል። ከ200 በላይ ንፁሀን ከሙሱ እና ጋዴድ ቀበሌዎች ተፈናቅለው ወደ ሀርለጎ ቀበሌ ሲገቡ ከ100 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ወደ አሙሩ መሳደዳቸው ተገልጧል። ኦነግ ሸኔ እና ደጋፊችም አማራውን በማፈናቀል ሀብት ንብረቱን እየዘረፉ መሆኑን የገለፁት ነዋሪዎች ለማስታረቅ በሚል የተሄደበትን መንገድም የሴራ አካሄድ መሆኑን ቀድሞ መረዳት አስፈላጊ ነበር ሲሉ ወቅሰዋል። አሁንም መንግስት መከካከያ እና የፌደራል ፖሊስ በመላክ በአማራ ላይ እየተፈፀመ ያለውን ግድያ፣እገታ እና ዝርፊያ በአስቸኳይ እንዲያስቆም ጠይቀዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply